Connect with us

ጋዜጣዊ መግለጫ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ጋዜጣዊ መግለጫ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ህግና ስርዓት

ጋዜጣዊ መግለጫ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር

የጅምላ እስራት (Mass-Arrest)፣
የስቪል ሰዎች ግድያ፣
ህዝብን ለይቶ የብዙሃን መገናኛ አገልግሎቶችን ማቋረጥ፣
ተማሪዎችን ለይቶ ከዩንቨርሲቲ ማበረር፣
ወታደራዊ አስተዳደር (command post) እና
በአጠቃላይ በ2012 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ዋዜማ ላይ በኦሮሚያ እየተፋፋመ ያለዉ ፖለቲካዊ አፈና በእጅጉ ያሳስበናል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በሀገሪቱ ዉስጥ የህዝቦች ነፃነት እና የድሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እዉን ለማድረግ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጀመረ ዓመት ከመንፈቅ ሆኖታል፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕዉቅና ሰርተፊኬት ካገኘ ግን ገና 3 ወሩ ነዉ፡፡ ባሳለፍናቸዉ ጊዜያት በመንግስት እና በገዢ ፓርቲ አላስፈላጊ ፖለቲካዊ ጫናዎች እየደረሰብን መሆኑን በተለያያ ጊዜያት ድምፃችንን ስናሰማ መቆየታችን የምታወስ ነዉ፡፡ ብሆንም ግን በተለያያ መልኩ ስደርስብን የነበረዉን ጫና በሙሉ በትግስት እና በብስለት በመየዝ ከመንግስትም ሆነ ከገዢዉ ፓርቲ እንድሁም ከሚመለከታቸዉ አካላትም ጋር በመነጋገር መፍቴ እያፈላለግን እስከ አሁን ዘልቄናል፡፡ የሉብንን የፖለቲካ ችግሮችን ለመቅረፍ የተሻለ መፍቴ ልሆን ይችላል በሚል፤ የ2012 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ታአማኒ እና ድሞክራሲያዊ ሆኖ ህዝቦች ነፃ ሆኖ ተወካዎቻቸዉን በሁሉም ደረጀ የምመርጡበት ምርጫ ይሆናል ብለን ተስፋ በማድረግ የረሳችንን ድርሻ ለመወጣት እየሰራን ነዉ፡፡

እንደምታወቀዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2012 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ዋና ዋና ቀናት እና ተግባራት የጊዜ ሰሌዳ (time table) ይፋ አድርጓል፡፡ በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከኛ የሚጠበቀዉን ሁሉ አሟልተን በምርጫዉ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ጥረት እያደረግን ብሆንም በመንግስት በኩል በአባላቶቻችን እና በደጋፊዎቻችን ላይ እየደረሰ ያለዉ ጫና ግን ከቀን ተቀን እየጨመረ እና እየከፋ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡

እየደረሰብን ያለዉን ጫና በአጭሩ ጨምቀን ስናስቀምጥ እንደሚከተለዉ ይሆናል፡
1. በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ማለትም ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ቡኖ ቤዴሌ እና እሉ አባ ቦራ በህግ ባልተደነገገ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወታደራዊ አስተዳደር (Command Post) ሥር ከወደቀ ከዓመት በላይ ሆኖታል፡፡

2. በወታደራዊ አስተዳደር (Command Post) ሥር ባሉት አከባቢዎች ሰዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ መብታቸዉ የተገደበ ከመሆኑም ባሻገር በቄለም ወለጋ፣ በምዕራብ ወለጋ እና በሁለቱም የጉጂ ዞኖች ጦርነትን አመኸኝቶ ግድያ፣ ዘረፋ፣ እስራት እና የግለሰቦችን ቤት እና ንብረት በማቃጠል ማጋየት ወዘተ በሰላማዊ ሲቪል ሰዎች ላይ ከምን ጊዜዉን በላይ በከፋ መልኩ የህዝባችንን ህይዎት ሰቆቃ ዉስጥ ከቷል፡፡ በተለየ መልኩ ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት ሁለቱ የወለጋ ዞኖች ላለፉት አንድ ወር ተኩል እንደ ስልክ፣ ኢንተርኔት የመሳሰሉ የብዙሃን መገናኛ አገልግሎቶች ጭምር በመቋረጡ የሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ሁላ አዳጋች ሆኖብናል (ይህን ጉዳይ አስመልክተዉ ከወር በፊት መግለጫ የሰጠንበት መሆኑ ይታወሳል)፡፡ ሆኖም ጉዳዩ እስከ አሁንም ጭምር መሻሻል አላሳየም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎት ከፊንፊኔ በስተ ምዕራብ በቅርበት በሉት አከባቢዎችም ጭምር እየተስፋፋ ይገኛል፡፡

3. የወታደራዊ አስተዳደሩ (Command Post) ችግር እንዳለ ሆኖ፤ ሰሞኑን ባልታወቀ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የጅምላ እስራት በዘመቻ መልኩ በኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ ይህን የጅምላ እስራት እየፈጸመ የለዉ አካል የኦሮሚያ ፖሊስ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ ይህ የጅምላ እስራት በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን እጅጉኑ የከፋ መሆኑም ታዉቋል፡፡ በመሆኑም ከአንድ ሳምንት ወድህ ብቻ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች (በ7 የኦሮሚያ ዞኖች እና በ26 ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች) በጅምላ ከታሰሩት አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን መካከል እስከ አሁን ባገኛነዉ መረጃ መሰረት ወደ 350 የሚጠጉ የታሰሩ ሲሆን በተጨባጭ በእጃችን የገቡት የ174 ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

I. በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
ከሰበታ፡
56 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸዉን መረጃ ያለን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ የደረሰን የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1. አቶ ጫላ ሰርዳ – የሀገር ሽማግሌ
2. አቶ ተሾመ ብቅላ – የሀገር ሽማግሌ
3. አቶ አንጋሳ ገረሱ – የሀገር ሽማግሌ
4. ተስፋ ሰንበታ
5. ዮሴፍ ያደታ
6. ሰቦና ባይሳ
7. አመድኑር አማን
8. ደጀኔ ጌታቻዉ
9. ታሪኩ አበባ
10. አቤቤ ድሳሳ

11. አብዲ ረጋሳ
12. ገዳ አሰፋ
13. በየና ገረሙ
14. ሳጅን ሚደግሳ
15. አብዲ ሄበኑ
16. ኢብራህም አሊ
17. ረብራ ደበሬ
18. ሰኚ ኩምሳ
19. ፈልመታ ኩምሳ
20. በያን ጀማል

21. አበራ በቀላ
22. ወንድሙ ተሾመ
23. ብራኑ ቦካ
24. ምስጋኑ ገለታ
25. ሰኚ አሰፋ
26. ጫላ ገረሙ
27. ደበላ ብራቱ
28. ኑሬ ሞሃመድ
29. ጉታ መገርሳ
30. ጉታ ሰቦቃ
ከቡራዩ፡

150 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸዉን መረጃ ያለን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ የደረሰን የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1. ሂካ ቡልቻ – የኦነግ ቡራዩ ጽ/ቤት ካድሬ
2. መልካሙ ገመቹ – መምህር
3. ንሞና ሻፊ
4. ቀበና ኢተፋ – ከነሙሉ ቤተሰቡ
5. ያደሳ ገብሳ
6. ከድር ቶለሳ
7. ተማም ሞሃመድ
ከለገጣፎ ለገዳዲ፡
1. አብርሽ ሻፊ
2. ኤፍሬም አምቦምሳ
3. ጃለታ ቶለሳ
4. አበያ ቦጃ
5. በርሲሳ አብዲ
6. ጅግሳ
7. ሞስሳ

ከጫንጮ፡
ብዙ ሰዎች መታሰራቸዉን መረጃ ያለን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ የደረሰን የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1. ግርማ ነጋሳ
2. ደረባ ግዛዉ
3. አሰፋ ነጋሳ
4. ጋድሳ አደሬ

II. ከምዕራብ ሸዋ ዞን
ከአምቦ ከታማ፡
1. መምህር ተሰማ ሀምብሳ
ከጨልያ፡
1. ታምሩ አለማየሁ
2. ደለሳ አበራ
3. በቀላ ጋሹ
4. ብቅላ አዱኛ
5. ድሪባ አመኑ
6. ጋሹ ፉርዶሳ
7. አዱኛ ብርሃኑ

ከባኮ ትቤ፡
1. ፍቃዱ ታደሳ
2. ያሬድ ድሩ
3. እሸቱ አዱኛ
4. ጋድሳ ጉተማ
ከጊንጪ፡
1. ሰኚ ግርማ
2. ዋቁማ ከሚል
3. ለታ ከበዳ
4. ለሚ ቱጆ
5. ባይሳ

ከጮቢ፡
1. ሌንሳ ከበዳ
2. ጫላ አብደታ
ከአደአ በርጋ፡
1. ባትሬ ተስፋዬ
2. መኮንን አለሙ
3. ኩባ ገመዳ
4. ዳንኤል መኮንን
5. ተስፋዬ ድባባ
6. በቀላ ድባባ
7. አራርሳ ደቻሳ
8. ደረጄ ቶለሳ
9. ዲነራስ
10. መንግስቱ

11. አሳምኖ አሰፋ
12. አማን በዳዳ

ከጀልዱ፡
1. ከበዳ ሂርኮ – መምህር
2. ተሾመ ሆርዶፋ – መምህር
3. ቶሌራ ጫላ – መምህር
4. ደጀኔ ሞስሳ – መምህር
5. አይናለም ለማ- መምህር

ከዳኖ፡
1. ገመዳ ተሾመ – የጽ/ቤት ፀሐፊ
2. ተስፋዬ ሆርዶፋ
3. ሃጫሉ ጎበና

III. ከሰሜን ሸዋ ዞን
ከዳኖ፡
1. ቶኩማ ገብሳ
2. አብዲሳ ጋሪ
3. ተሾመ ነጋሳ
4. ደበላ ፈይሳ
5. ፍቃዱ
ከኤጄሬ፡

17 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸዉን ያረጋገጥን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ አልደረሰንም፡፡
ከአቡና ግንደበረት፡

5 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸዉን ያረጋገጥን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ አልደረሰንም፡፡

IV. ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን
ከአሙሩ፡
1. ተስፋ ቶሌራ – መምህር
2. አሰፋ ዋቅጅራ
3. መለሳ እንዳለ
4. ጃርሶ አለሙ
5. ፍቃዱ ሁሉቃ
6. ደሶ ቶሌራ
7. ብቅላ አብዲሳ
8. አየላ ገመቹ
9. ሀብታሙ አብዲሳ
10. ልክሳ ገነቲ

11. ከፍአለ ነጋሳ
12. ታከለ ነጋሳ
13. ባቤ ድንሳ
ከአባይ ጮመን፡
1. ጋድሳ ሆርዶፋ
2. ደስታ ደጀኔ
3. ጌቱ ከበደ
4. ባይሳ ጉደሌ – በከባድ የአካል ድብደባ የተጎዳ

V. ከኢሉ አባቦራ ዞን
ከዳሪሙ፡
1. ጫርቦሳ ከበዳ
2. መሳ ሞሌ
3. አጅቦ ዳዉድ
4. ተፈሪ ተካልኝ
5. በኪር ኡመር
6. ልጃቡ ሙስጠፋ

ከመቱ ዩኒቨርሲቲ፡
1. ቦንሳ ኩመራ
2. አባይ አለሙ
3. ኤባ አዳሙ
4. አኑዋር ሱፍያን
5. ኩኒስ ሙክታረ
6. አብዱበ ገርብቻ
7. እብሳ ሙሳ
8. አሊሀጂ ጃርሶ
9. ጉዮ ጃርሶ
10. ኑረዲን ሱፍያን

ከቡሬ፡
1. ሲነን ሁሴን
2. አማኑኤል ቡሊ
3. ለልሳ አመኑ
4. ናኦል አዳና
5. ፍራኦል አዳነ
6. ምንተስኖት አበበ
7. አሸናፊ ፀጋዬ
8. አነሶ ኢብራህም
9. ተመስጌን ገበዮ

ከሀሉ እና ኖጳ፡
1. በርሲሳ ፋንታ
2. ሱባሎ ጌታቸዉ
3. ሙሉቀን ተስፋዬ
4. ፍራኦል ደረጄ
5. እንዳለ ዘዉዴ
6. አንዱአለም ገዛኝ
7. ወርቁ ጥላሁን
8. ለልሳ በፍቃዱ
9. ዳንኤል ታደሳ
10. መልካሙ ረታ

ከመቱ ከተማ፡
ብዙ ሰዎች መታሰራቸዉን ያረጋገጥን ስሆን፤ የስም ዝርዝራቸዉ የደረሰን፡፡
1. መምህር ዳግም ወርቅነህ – የመቱ የኦነግ ጽ/ቤት ፀሐፊ

VI. ከባሌ ዞን
ከሮቤ ከተማ፡
1. አብዲ ሞሃመድ
2. ጄቲ ሁሴን
3. ሌንጮ ጀዋሮ

ከደሎ መና፡
1. ሐሰን ሞሃመድ
2. አልይ ሞሃመድ ሐጂ
3. ጅብሪል ዋቶ
4. አብድርሹኩር ማልም
5. ሁሴን ሼክ አህመድ
6. አብዱ ሞሃመድ-ሁሴን
7. ከሚል አቡበከር
8. አዴ እስቱ

VII. ከምዕራብ ሐረርጌ
ከገመቺስ ወረዳ፡
1. ከድር ሁሴን
2. ብልሱማ አህመድ
3. ጃፈር አብዶ
4. እድርስ ሸመጤ
5. ጃፈር ሁሴን
6. ጀማል ኑራ እንድሬ – የኦነግ ጽ/ቤት ኀላፊ
ከኦዳ ቡልቱም፡
1. ወ/ሮ ሻሺ ሳድቆ
2. አብዶ ስራጅ – የኦነግ ጽ/ቤት ምክትል ኀላፊ
3. ሄይደራ አህመድ
4. መርሻ እንዳለ
5. ዝያዶ ሳኒ
6. ኦብሳ ኑሬ

ከዶባ፡
1. አብደላ አህመድ
2. መገርሳ ሞሃመድ
3. ሙሳ ሞሃመድ
4. ቶፍቅ አልይ አብዲ
5. ከድር ረሺድ
6. ቃስም ኡመሬ

VIII. በተጨማሪም፡
በቀን 02/02/2012 ዓ.ም በምዕራብ ሐረርጌ ዶባ ወረዳ ብዮ ከራባት በሚትባል ከተማ የኦሮሚያ ፖሊሶች ወጣቶችን በጅምላ በመደብደብ ከባባድ ጉዳት አድርሶባቸዉ በከተማዉ የሚገኛዉንም የድርጅቱን ጽ/ቤት ዘግቷል፡፡

እላይ የተጠቀሰዉ መረጃ ከዚህ በፊት በፊንፊኔ እና በተለያዩ ቦታዎች የታሰሩትን የኦነግ አባለትን እና ደጋፊዎችን አይጨምርም፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መፍቴ ይሰጥ ዘንድ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ያሳወቅን ስሆን ከመንግስት ጋርም በተገኘ አጋጣሚ በሙሉ ሳንመክርበት የተቆጠብንበት ጊዜ የለም፡፡

ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም የምርጫ ዋዜማ ላይ ሆና በኦሮሚያ ዉስጥ የነበረዉ ችግር ተቀርፎ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ዜጎች በሰላም እና በነፃነት የመንቀሳቀስ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ መምጣቱ እጅጉኑ እያሳሰበን መጥቷል፡፡
ስለሆነም አሁንም ተስፋ ሳንቆርጥ ትልቁን ኀላፍነት መወጣት ያለበት መንግስት፤ ይህን ችግር ከማባባስ ይልቅ መፍቴ ለማምጣት ይሰራ ዘንድ አሁንም ደግመን አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ፡-

1. የተጀመረዉ የጅምላ እስራት በአስቸኳይ እንድቆም፡፡
2. የታሰሩት በሙሉ መብታቸዉ በአግባቡ ተጠብቆላቸዉ በአስቸኳይ ህግን በተከተላ መልኩ ፍትህ እንድያገኙ እናሳስባለን፡፡
3. ለረጅም ጊዜ የተቋረጠዉ የብዙሃን መገናኛ አገልግሎት በቶሎ ወደ ቦታዉ እንድመለስ፤ ካልሆና ግን የህዝብን ስሜት ወደ አላስፈላጊ ቁጣ እንዳይገፋ እንሰጋለን፡፡

4. ካለ ህግ አግባብ የታወጀዉ እና የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት ወታደራዊ አስተዳደር (Command Post) ህዝባችንን ለአስከፊ ችግር በማጋለጡ በአቸኳይ እንድነሳ፤ እንድሁም በስቪል በዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ግድያ በአስቸኳይ እንድቆም እንጠይቃላን፡፡

5. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እየመጣ ያለዉን ሀገራዊ ምርጫ ለማሳካት ቀጥተኛ ተጠያቅነት እንዳለበት አዉቆ በምርጫዉ ዋዜማ እየገጠሙን የሉን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በአግባቡ በመስራት መፍቴ ለማምጣት ኀላፍነቱን ይወጣ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

6. የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሺንም በኦሮሚያ ዉስጥ እየተፈፀመ ያለዉን የሰባዊ መብት ረገጣን በመከታተል ተገቢዉን ሪፖርት እያቀረበ እንዳልሆነ ተገንዝበናል፡፡ ይህ ተቋም ኀላፍነቱን በአግባቡ እንድወጣ ማስታወስ እንወዳለን፡፡

7. ሉአላዊ መንግስታት እና የኢትዮጵያ አጋር መንግስታት በዚህች ሀገር ድሞክራሲ መሰረቱን ይጥል ዘንድ የተለያዩ ድጋፍ በማድረግ ላይ ያላቹ በሙሉ፤ በኢትዮጵያ ዉስጥ እየሄደ ያለዉ ሁኔታ ሀዲዱን የሳታ እና ፀረዲሞክራሲያዊ አካሄድን እየተከተለ ያለ መሆኑን ተገንዝባቹ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሀዲዱ ይመለስ ዘንድ ተገቢዉን ምክር እና ጫና በማድረግ የድርሻቹን ትወጡ ዘንድ እናሳስባቿለን፡፡

8. በአፍርካ ደረጃ የህዝቦችን እና የሰባዊ መብት አያያዝን የሚከታተል ኮሚሺን (African Commission on Human and Peoples right) በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች የሚያደርገዉን ክትትል፤ የኢትዮጵያ መንግስት እየሄደበት ያለዉን ፀረዲሞክራሲያዊ አካሄድንም በመከታተል ተገቢዉን ሪፖርት በማቅረብ የድርሻዉን ይወጣ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡

9. የኢትዮጵያ መንግስትም ሀዲዱን ስቶ ሀገሪቷን እየገፋበት ያለዉን የተሳሳተ መንገድ ተገንዝቦ ነገሮች ከቁጥጥር ዉጪ ሳይወጡ ቆም ብለዉ እራሱን እንድያይ እና የማስተካከያ እርምት እርምጃ እንድወስድ እናሳስባለን፡፡ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በሙሉ ባሳተፋ መልኩ በምክክር መፍቴ ያገኝ ዘንድ መድረክ እንድያመቻች አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

10. በኦሮሚያም ሆነ በመላዉ ሀገሪቱ ዉስጥ ሰላም እና መረጋጋት ተረጋግጠዉ በመጭዉ 2012 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ህዘቦች ነፃ ሆኖ ተወካዮቻቸዉን በመምረጥ ህዝበዊ መንግስት ይመሰርቱ ዘንድ ገዢዉን ፓርቲ ጨምሮ የሚመለከተን የባላድርሻ አካላት በሙሉ ኀላፍነታችንን እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ለታዩት ችግሮች የግንዛቤ ማስጫበጫ እና መፍቴ ለማስገኛት ማበርከት የምችሉት የተለያዩ አካላት ( የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች፤ የብዙሃን መገናኛ ፤ ጋዜጠኞች፤ ግለሰቦች እና ገምቢ ተጽኖ ማሳደር የምችሉ አካላት) በሙሉ ይህን ሁኔታ ተገቢዉን ትኩረት በመስጠት ገምቢ ሚና እንድጨወቱ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በበኩሉ ላሉት ችግሮች በሙሉ አስተማማኝ እና ዘላቅ መፍቴ ለማስገኘት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ድል ለሰፊዉ ህዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
የካቲት 06/2012 ዓ.ም

ማሳሰቢያ፡
ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠዉ ባለፈዉ ዓርብ የካቲት 6/2012 ዓ.ም. በኣፋን ኦሮሞ ስሆን የአማሪኛ ትርጉሙ ዘግይቶ በመድረሱ ይቅርታ እንጠይቃለን።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top