Connect with us

አጋቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አጋቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አጋቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የካቲት 3 ቀን 2012ዓ.ም አሽከርካሪ ኤርሚያስ ፈንታ በለጠ ከረዳቱ ዮሴፍ ባበይ ጋር በኮድ 3-31298 አ.አ በሆነ fsr የጭነት ተሽከርካሪ እንጨት ጭነው ከጎንደር ወደ መተማ ሲጓዙ ከሌሊቱ 11፡30 ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ መግቢያ አካባቢ ተከሳሽ 1ኛ. ድንቁ አበበ ፈንታ ሁለት እግር ክላሽእንኮቨ ጠመንጃ 2ኛ. በዜ አለሙ ተሸመ ጀሌ 3ኛ. ያልተያዙ ሌሎች 5 የታጠቁ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን ተሸከርካሪውን በጥይት በመምታት አስቁመው ረዳትና ሾፌሩን አግተዋል፡፡

መረጃው የደረሰው የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ከአካባቢው ሚሊሻ ና መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል በታገቱበት ዕለት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጭልጋ ወረዳ ኩሻይና ቀበሌ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ታጋቾች ላይ ጉዳት ሳይደርስ መለቀቃቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኮሚኒኬሽን ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ውብነህ አስናቀ ገልዋል፡፡

እንደ ኮማንደሩ ገለፃ በተኩስ ልውውጡ ከአጋቾች 5ቱ የታጠቁት ያመለጡ ሲሆን የተያዙት ሁለቱ የምርመራ መዝገብ በፍጥነት ተጠናቆ ለጭልጋ ወረዳ ፍ/ቤት ተልኮ ፍ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ከረፋዱ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባልተያዙት ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ውብነህ ፖሊስ የህበረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲረጋገጥ ለሚያደርገው ጥረት ህበረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(አማራ ፖሊስ ኮምሽን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top