Connect with us

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ የ217 ካምፓሶችን ፈቃድ አገደ

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ የ217 ካምፓሶችን ፈቃድ አገደ
Photo: Facebook

ወንጀል ነክ

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ የ217 ካምፓሶችን ፈቃድ አገደ

በአጠቃላይ 497 ካምፓሶች በ1045 የስልጠና መስኮች የዕውቅና ፈቃድ ጥያቄ ለኤጀንሲው አቅርበው የነበረ ቢሆንም ኤጀንሲው መስፈርቱን አሟልተው ባለመገኘታቸው ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉን ገልጿል።

በ217 ካምፓሶች የቀረቡ 478 የስልጠና መስኮች የሚጠበቅባቸውን መስፈርት ባለማሟላታቸው የዕውቅና ፈቃድ እንዳልሰጣቸው እና በኤጀንሲው ግምገማ መሰረት በ567 የስልጠና መስኮች ተገቢውን መስፈርት አሟልተው የተገኙ 280 ካምፓሶች ብቻ የእውቅና ፍቃድ ማግኘታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡

በ283 የስልጠና መስኮች 132 ካምፓሶች የዕውቅና ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ኤጀንሲው በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

ከነዚህ ውስጥም በ196 የስልጠና መስኮች ተገቢውን መስፈርት አሟልተው የተገኙ 85 ካምፓሶች የእውቅና ፈቃድ ዕድሳት ማግኘታቸውን ኤጀንሲው ለጣቢያችን ከላከው ሪፖርት ላይ ተመልክተናል፡፡

በ87 የስልጠና መስኮች መስፈርቱን አሟልተው ያልተገኙ 47 ካምፓሶች ደግሞ የዕውቅና ፈቃድ ዕድሳት ሳያገኙ ቀርተዋልም ብሏል፡፡

በጥቅሉ የእውቅና ፍቃድና እድሳት ጥያቄ ያቀረቡ 629 ካምፓሶች እና 1 ሺ 328 ፕሮግራሞች በኤጀንሲው በኩል መስተናገዳቸውን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ትኩስ ዜናዎችን፣ መረጃዎች እና ሌሎች የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ስርጭቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

(ኢትዮ ኤፍኤም)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top