Connect with us

ምርጫ ቦርድ፣ በጀዋር መሐመድ የዜግነት ጉዳይ ኤጀንሲው እስከመጪው ሰኞ ዕለት ድረስ ማብራሪያ እንዲሰጠው አዘዘ

ምርጫ ቦርድ፣ በጀዋር መሐመድ የዜግነት ጉዳይ ኤጀንሲው እስከመጪው ሰኞ ዕለት ድረስ ማብራሪያ እንዲሰጠው አዘዘ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ምርጫ ቦርድ፣ በጀዋር መሐመድ የዜግነት ጉዳይ ኤጀንሲው እስከመጪው ሰኞ ዕለት ድረስ ማብራሪያ እንዲሰጠው አዘዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቶ ጀዋር ሲራጅ መሐመድ ዜግነት ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ደብደቤ ጻፈ፡፡

ቦርዱ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥር አ1162/11/18/07 በጻፈው በዚሁ ደብዳቤ ኤጀንሲውን ማብራሪያ የጠየቀው በአዋጅ ቁጥር 378/1996 አንቀጽ 22 ላይ በሰፈረው ድንጋጌ መሠረት አንድ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የሌላ አገር ዜግነት ያለው ሰው መደበኛ ኑሮውን በኢትዮጵያ ካደረገ፣ የሌላ አገር ዜግነቱን ከተወ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን እንዲመለስለት ለባለሥልጣኑ ካመለከተ የኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለኤጀንሲው ውሳኔ ወዲያውኑ ያገኛል ወይንስ አያገኝም የሚለው ጉዳይ ላይ ነው፡፡

ቦርዱ በዚሁ ደብዳቤ ኤጀንሲው እስከ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ ማብራሪያ እንዲሰጥ ወይንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሰጠው ውሳኔ ካለ እንዲያሳውቅ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7(3) መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመመዝገብ የመከታተል እና የመቆጣጠር ሥልጣኑን መነሻ በማድረግ የአሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አባል ሆነው በቅርቡ የተቀላቀሉትን አቶ ጀዋር ሲራጅ መሐመድ የኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ በማግኘት ሒደት ላይ ነኝ እያሉ አባል አድርጎ “ኢትዮጵያዊ” የሚል የአባልነት መታወቂያ ከመስጠቱ ጋር ተያይዞ ፓርቲው በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥ በቦርዱ ቀደም ሲል ታዞ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ፓርቲው አቶ ጀዋር መኖሪያቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመሰረቱ፣ ይዘውት የነበረውን የሌላ አገር ዜግነት ስለተው፣ የኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዲመለስላቸው ሥልጣን ላለው አካል ስላመለከቱ የኢትዮጵያዊ ዜግነት አግኝተዋል በማለት ምላሽ መስጠቱን ቦርዱ በደብዳቤው አስታውሷል፡፡( የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከዚህ ዜና ጋር ተያይዟል)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top