ኖቭል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሳምንታዊ መግለጫ
ዓለም አቀፍ መረጃ፡
• በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት፣ እስከ ጥር 28/2012፣ ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ምሳ ሁለት (30,852) ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ጥር 29/2012 ድረስ ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት (635) ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ፡፡
ሀገራዊ መረጃ
• እስከአሁን ድረስ 29 ጥቆማዎች በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ ለሚገኘው የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰዋል፡፡ 29ኙ ላይ በተደረገው ማጣራት፣ 14ቱ ምልክቶች ያሳዩ ስለነበረ (suspected cases ) ፤ በሽታው እንዳለባቸው ወይም እንሌለባቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ወደ መቆያ ስፍራ (Isolation center) እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ 11 ናሙናዎች ተልከው ስምንቱ (8) ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ 3 ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የምርምራው ውጤት እየተጠበቀ ሲሆን በቀጣዬቹ ቀናት 3 ናሙናዎች ለምርመራ የሚላኩ ይሆናል፡፡
• በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት፣ እስከ ጥር 28/2012፣ ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ምሳ ሁለት (30,852) ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ጥር 29/2012 ድረስ ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት (635) ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ፡፡
• ከቻይና ዉሃን ከተማ የሚመጡ ማናቸውም መንገደኞች ወደ ለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲገቡ ተወስኗል በመሆኑም ወደ ሀገር እንደገቡ በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው አስፈላጊው የህክምና ክትትል የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡
• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ከሌላው መንገደኛ ጋር ሳይቀላቀሉ የሙቀት ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን በተጨማሪም ከቻይና ለሚመጡ መንገደኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የኢሚግሬሽን ልዩ መስኮት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡
• ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የጤና ሁኔታ መከታተል እንዲቻል ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቶ አገልግሎቱም ተጀምሯል፡፡
• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለሚሰሩ ሁሉም አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር