Connect with us

ስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም.ይጀመራል

ስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም.ይጀመራል
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም.ይጀመራል

ለሀገር እና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት በ2012 ዓ.ም ለሚያካሄደው ስምንተኛው መርሐ ግብሩ የእጩዎችን ጥቆማ ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም አንስቶ ከህዝብ መቀበል ይጀምራል፡፡

ለዚህ የሽልማት መርሐ ግብር ከዚህ በታች በተገለጹት አስር ዘርፎች ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የእጩዎች ጥቆማ እንቀበላለን፡፡

1. መምህርነት
2. ሳይንስ (ህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ምህንድስና፣
ኬሚስትሪ፣ አርክቴክቸር፣ ወዘተ)
3. ኪነ ጥበብ/ሥነ-ጥበብ፣ (በወግ ድርሰት)
4. በጎ አድራጎት (ርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት)
5. ቢዘነስና ሥራ ፈጠራ
6. መንግሥታዊ የሥራ ተቋማት ኃላፊነት
7. ቅርስና ባህል
8. ማኅበራዊ ጥናት
9. ሚዲያና ጋዜጠኝነት
10. ለኢትዮጵያ እድገት አስተዋጽዖ ያበረከቱ ዳያስፖራዎች፤

ካለፈው ዓመት ሰባተኛው የበጎ ሰው ሽልማት አንስቶ በሽልማት ዘርፎች ውስጥ የተካተተው ለአገራችን እድገት አርአያነት ያለው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ዳያስፖራዎች እውቅና የሚያገኙበትን ዘርፍ ጨምሮ እስካሁን ሥራ ላይ ባዋልናቸው ዘርፎች በሙሉ ጥቆማ እንቀበላለን፡፡

በተለይ የማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት በቂ እጩዎች ባለመጠቆማቸው ሽልማቱ ስላልተካሄደ፣ በዚህ የሙያ ዘርፍ ያሉ ደርዝ ያለው ሥራ የሠሩ ኢትዮጵያውያንን ለማክበርና አርአያነታቸውን ለማጉላት ሕዝቡ በተለይም ለሙያው ቅርብ የሆኑ ሁሉ ጥቆማቸውን እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

እንዲሁም በኪነ ጥበብና ሥነ ጥበባት ዘርፍ በዘንድሮው መርኀ ግብር ከሥነ ጽሑፍ መስኮች አንዱ በሆነው የወግ ድርሰት ላይ እናተኩራለን፡፡ የወግ ድርሰት ኢልቦለዳዊ በሆነ የሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የሚመደብ ጥበባዊ በሆነ የአጻጻፍ ብቃት የሚቀርብ ሲሆን በርካታ አንጋፋና ወጣት ደራሲያን የድርሰት በረከታቸውን አቅርበውበታል፡፡ ስለዚህ የዘርፉን ጥበባዊነት ለማጉላትና ደረሲያኑንም ለማበረታታት የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ መስክ ተደርጎ ተመርጧል።

ባለፉት ሰባት የሽልማት ወቅቶች፤ አገራችን የምትኮራባቸውና የላቀ አርአያነት ያለው ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን እውቅና የሰጠነው ከህዝብ በቀረቡ ጥቆማዎች መሰረት ነው፡፡ የበጎ ሰው ሽልማትን ለዚህ ያበቃውም በሽልማቱ ሂደት በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የህዝብ ተሳትፎ በመኖሩና ይህም ከዓመት ዓመት እያደገ በመሄዱ ስለሆነ ይህ ተሳትፎ አሁንም እንዳይለየን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ጠቋሚዎች እጩዎችን በሚጠቁሙበት ጊዜ እጩው ግለሰብ ለአገርና ለህዝብ ያከናወኑትን ተግባር በዝርዝር እንዲገልጹልንና የሚገኙበትንም አድራሻ እንዲጠቁሙን እናሳስባለን፡፡

ስለዚህ ይህን የበጎ ሰው ሽልማትን ዓላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከላይ በተገለጹት መስኮች ለጥቆማ በተመደበው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ህዝቡ ለዚህ ሽልማት ብቁ ናቸው የሚላቸውን እጩዎች እንዲጠቁም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ጥቆማ የምንቀበለው በስልክ፣ በቫይበር፣ በቴሌግራም፣ በኋትስአፕ፣ በኢሜይልና በፖስታ ነው፡፡ አድራሻዎቹም፤

ስልክ፡ 0977-23 23 23 (ቫይበር፣ ቴሌግራምና ኋትስአፕን ጨምሮ)
ኢሜይል፡ begosewprize@gmail.com
ፖስታ፡ 150035

የበጎ ሰው ሽልማት ዓላማ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ መልካም የሚሠሩ፣ ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በብቃትና በልዩ ልዕልና የሚወጡ፣ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለውጥ አምጪ ተግባር የፈጸሙ፤ በብዙ ሰዎች የማይደፈረውን ተግባር በተነሣሽነት የከወኑ፣ ለድጋፍ ፈላጊ የማኅበረሰብ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነት ወስደው የሠሩ፣ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባሕል፣ እንዲጠበቅ፣ የሀገሪቱ ሥልጣኔ ከፍ እንዲል የሠሩ ኢትዮጵያውያንን በማበረታታት፣ ዕውቅና በመስጠትና በመሸለም ሌሎችን በጎ ሠሪዎች ለሀገራችን ማፍራት ነው፡፡

ከሕዝብ የሚቀርበው ጥቆማ ከተጠናቀቀ በኋላ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ፣ ለመጨረሻው ውድድር ተመርጠው ስማቸው ለዳኞች የሚላከውን እጩዎች ማንነት፣ ሕዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ፤ አውቆም ለሀገርና ለሕዝብ ባበረከቱት አስተዋጽዖ እንዲያከብራቸው ዝርዝራቸውን በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ይፋ እናደርጋለን፡፡

የመጨረሻውን የየዘርፎቹን የበጎ ሰው ተሸላሚ ምርጫ የሚያደርጉት ለእያንዳንዱ የሽልማት ዘርፍ በዳኝነት የተመረጡ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ዳኞቹ በእውቀታቸውና በሙያቸው አንቱ የተባሉ፣ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውና በታማኝነት ምርጫውን ያከናውናሉ ተብለው የታመነባቸው ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ዘርፍም አምስት ዳኞች ተመርጠው ምርጫውን ያከናውናሉ፡፡

በጎ ሠሪዎችን በማክበርና በመሸለም ሌሎች በጎ ሠሪዎችን እናፍራ!

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top