Connect with us

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ
“ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል። የገደለም ፍርድ ይገባዋል።” ማቴዎስ 5:21

መንግሥት ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ አካላትን በማጣራትና ለሕግ በማቅረብ ተገቢውን ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርግ ዘንድ ቤተክርስቲያን አሳስባለች።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ አዲስ መቃኞ ቤተክርስቲያን መሠራቱን መነሻ በማድረግ በአካባቢው በሚገኙ ምዕመናንና በከተማው የጸጥታ አካላት መካከል ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 በተፈጠረው አለመግባባት የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋትና የተጎዱ ሰዎችን መነሻ በማድረግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መግለጫ ሰጥተዋል።

ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል። የገደለም ፍርድ ይገባዋል። የማቴዎስ ወንጌል 5:21 ኃይለ ቃልን መነሻ ያደረጉት ቅዱስ ፓትርያርኩ የከተማው አስተዳደርና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ዝርዝር ጉዳዩን በማጣራትና ለተፈጸመው ችግር ተጠያቂ የሆኑትን አካላት ለሕግ በማቅረብ ተገቢውን ውሳኔ እንዲያገኙ እንዲደረግና የወንጀል ምርመራ የማጣራት ሂደቱን አስመልክቶ ዝርዝር ሪፖርት ለሕዝቡ ይፋ እንዲደረግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

እንዲህ ዓይነቱ ክስተት በሚፈጠርበት ጊዜ የግራ ቀኝ ወገኖች በሰከነና በሰለጠነ መንገድ ችግሩን በውይይት መፍታት ሲገባ ወደ ኃይል እርምጃ መገባቱና የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ቤተክርስቲያኒቱን በእጅጉ እንዳሳዘናት ቅዱስ ፓትርያርኩ አክለው ገልጸዋል።

በመጨረሻም በተፈጠረው ችግር ለሞቱት ወገኖች እረፍተ ነፍስን እንዲሰጥ : ለሟች ቤተ ሰዎችም መጽናናት እንዲያድል በመጸለይ: የተፈጠረው ግጭት እንዲረግብና ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ በማቅረብ መግለጫውን አጠናቀዋል።

ጥር 27 ቀን 2012 ዓ/ም
አዲስ አበባ

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top