Connect with us

ይድረስ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ – ተፃፈ ከህወሓት

ይድረስ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተፃፈ ከህወሓት
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ይድረስ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ – ተፃፈ ከህወሓት

ይድረስ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ተፃፈ ከህወሓት

ቦርዱ ተሰብስቦ በትላንትናው ዕለት ያሳለፈውን ውሳኔ ደርሶን ተመልክተነዋል።
ቅሬታችንን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

1ኛ.ቦርዱ በውሳኔው ድርጅታችን ኢህአዴግ ፈርሶ በብልፅግና ፓርቲ ተተክቷል ማለቱን አጥብቀን እንቃወማለን። ትክክለኛ ወራሾቹ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመራችን ንቅንቅ ያላልነው፣ በዚህ ምክንያት በአንዳንድ ጓዶቻችን “ተቸካይ” ተብለን የተወረፍነው እኛ ህወሓቶች መሆናችንን ዓለም የሚመሰክረው ሐቅ ሆኖ ሳለ ይህ መካዱ ቅር አሰኝቶናል፣

2ኛ.ውርሱ ይመለከተናል ያሉት የገዛ ልጆቻችን በህይወት መኖራችንን መካዳቸው ሳያንስ፣ ቦርዱ በቁማችን ለወረሱን ልጆቻችን የገዛ ሐብታችንን ያከፋፈለበት አድሎአዊ ቀመር ግልፅነት የጎደለው ሆኖ አግኝተነዋል፣ ውሳኔውም የውርስ ሐብት ህጉን የሚጥስ ነው፣

3ኛ.እኛ ህወሓቶች የኢህአዴግን መስመር ማስቀጠላችን፣ የታላቁ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተአለም ወራሽ መሆናችንን ቦርዱ ግምት ውስጥ ሳያስገባ፣ ግብራችንን ንቀው፣ ስማችንን ብቻ ለወረሱት ልጆቻችን አድልኦ ማሳየቱ ተገቢ ነው ብለን አናምንም፣
በአጠቃላይ ለቦርዱን የምናቀርበው አቤቱታ:-

1ኛ.የእኛ ወላጆችን በህይወት መኖር ግምት ውስጥ ሳይገባ በቁማችን እንድንወረስ የተሰጠው ኢ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲነሳልን፣

2ኛ.የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመራችን እያስቀጠልን በመሆኑና በቅርቡም የፌደራሊስት ሀይሎች ግንባር የኢህአዴግን መስመር ስለሚተካ እስከዚያው ውሳኔው እንዲዘገይልን፣

3ኛ. ከምንም በላይ የዛሬ የቁም ወራሽ ልጆቻችንን ለማሳደግ ላለፉት 40 አመታት ያሳለፍነው ውጣውረድ፣ የዓመታት ድካምና ልፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ልጆቻችንን ከቁም ውርስ እንዲነቅልልን እንጠይቃለን።

አብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመራችን ዛሬም የብሔር ብሔረሰቦች ዋስትና ነው!!
የማይነበብና ማሀተምና ፊርማ አለው።
የሥራ አመራር ኮምቴ

(ምናባዊ ፍተላ ~ ከጫሊ በላይነህ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top