Connect with us

ምርጫ ቦርድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መፍረሱን አረጋገጠ

ምርጫ ቦርድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መፍረሱን አረጋገጠ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ምርጫ ቦርድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መፍረሱን አረጋገጠ

ምርጫ ቦርድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መፍረሱን አረጋገጠ
~ የህወሓት የንብረት ክፍፍል ይገባኛል ጥያቄ ላይ ውሳኔ አሳለፈ

ኢህአዴግ በሊቀመንበሩ በኩል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ግንባሩ መፍረሱን ለቦርዱ ያሳወቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) በሊቀመንበሩ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ግንባሩ በመፍረሱ የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የግንባርን መፍረስ የመወሰን ስልጣን የቦርዱ በመሆኑ ግንባሩም ሆነ ህወሃት ግንባሩ መፍረሱን መጥቀሳቸው የማይገባ ቢሆንም ቦርዱ ሁለቱ ሊቃነመናብርት ያቀረቧቸውን የጽሁፍ ጥያቄዎ መሰረት በማድረግ ግንባሩ መፍረስ አለበት ወይ? ከፈረሰስ ውጤቱ ምን ይሆናል በሚል ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ የግንባሩ አባል ሶስት ፓርቲዎች ከግንባሩ ወጥተው አዲስ ውህድ ፓርቲ መመስረታቸውን የብልጽግና ፓርቲን አመሰራረት ከሚያሳየው መዝገብ ተረድቷል፡፡ በመሆኑም ግንባሩ በተግባር መፍረሱን ቦርዱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ የግንባሩ መፍረስ ተከትሎ ቦርዱ የኢህአዴግን ንብረት አስመልክቶ ውሳኔ መስጠት እንደሚያስፈልግም ተረድቷል፡፡

በመሆኑም የኢህአዴግ አባል ድርጅት የነበሩት ሶስቱ ማለትም አዴፓ ኦዴፓ እና ደኢህዴን ብልጽግና የሚባል ፓርቲ መመስረታቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ህወሃት ህልውናውን ጠብቆ የቆየ ፓርቲ በመሆኑ በህጉ መሰረት በብልጽግና እና በህወሃት መካከል የኢህአዴግን ንብረት ክፍፍል ማድረግ እንደሚገባ ቦርዱ ተገንዝቧል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ የኢህአዴግን ንብረት አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል፡፡

1.ብልጽግና እና ህወሃት የኢህአዴግ ንብረትና ሂሳብ የሚያጣራ አጣሪ በጋራ እንዲሰይሙ

2.በኢህአዴግ ስም ያለ ማናቸውም እዳ ተጣርቶ እንዲከፈል

3.ከእዳ ክፍያ ቀሪ የሆነ ሃብት 3/4ተኛው ለብልጽግና ፓርቲ ( የሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውህደት በመሆኑ) ¼ተኛ ደግሞ ለህወሃት ድርሻ መሆኑ ታውቆ በዚያ መሰረት ክፍፍል እንዲያጠናቅቁ

4.ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በህጉ መሰረት በ6 ወር ውስጥ ለቦርዱ እንዲያሳውቁ ተወስኗል፡፡ (ውሳኔው በጽሁፍ የሚደርሳቸው ይሆናል)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top