Connect with us

አደራ የበላው በእስራት ተቀጣ

አደራ የበላው በእስራት ተቀጣ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አደራ የበላው በእስራት ተቀጣ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 669(2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የንብረት ስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በቀረበበት ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡

በዐቃቤ ሕግ በቀረበው የክስ መዝገብ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው ተከሳሽ ግዛቸው ገነነ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 669(2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፤ እንዲሁም በአማራጭ የክስ በማጠናከሪያነት በቀረበበት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 702(2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በውል ግዴታ የሌለውን ሰው ንብረት እንዲጠብቅ አደራ ተቀብሎ እያለ ተከሳሽ ከሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ነሀሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ዋአካና ባርና ሬስቶራንት ግቢ ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ በመስራት ላይ እያለ ንብረትነታቸው የዚሁ ባርና ሬስቶራንት የሆኑትን በአጠቃላይ ብር 194,000 (አንድ መቶ ዘጠና አራት ሺህ ብር) የሚገመቱትን የተለያዩ ንብረቶች ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመኪና ጭነው የወሰዱ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀል ሊከሰስ መቻሉን የቀረበበት የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ክሱን የተመለከተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቂርቆስ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃ አስተባብሎ እራሱን እንዲከላከል ቢያዝም ተከሳሽ ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ተመልክቶ በተከሳሹ ግዛቸው ገነነ ላይ ጥር 05/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት 8 አመት ከ6 ወር የእስራት ቅጣት ወስኖበታል፡፡(ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top