Connect with us

22 አካባቢ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

22 አካባቢ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

22 አካባቢ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ማክሰኞ ምሽት 22 አካባቢ ከቤተክርስቲያን ግንባታ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ኢ/ር ታከለ ኡማ ክስተቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው አስተዳደሩ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እስካሁንም ከጥፋቱ ጋር ግኑኝነት አላቸው በሚል የተጠረጠሩ አመራሮችን ጨምሮ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማጣራቱም እንደቀጠለ ገልጸዋል፡፡

ከጥፋቱ ጋር በተያያዘ የተደራጁ መረጃዎች እየተገኙ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ፡፡

አስተዳደሩ ከምንጊዜው በላይ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ኢ/ር ታከለ በተለይም ከኃይማኖት ተቋማት ይዞታ ጋር በተያያዘ አፋጣኝ ምላሾች እየተሰጡ እንደሆነ ችግሮች ሲኖሩም በመነጋገር እየተፈቱ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት ምሽትም የኃይማኖት ተቋሙ የተገነባበት ቦታ ተገቢ ባይሆንም በለሊት ለማፍረስ መኬዱ ተገቢ ባለመሆኑ ትእዛዝ የሰጠው አካል ላይ ማጣራት እየተደረገ እንደሆነና ተገቢው እርምጃም እንደሚወሰድ እንዲሁም ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ኢ/ር ታከለ፡፡

በጥፋቱ ህይወታቸውን ያጡ ወጣቶች ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን የተመኙት ኢ/ር ታከለ የተጎጂ ቤተሰቦችን የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡(አ/አ ከንቲባ ፅ/ቤት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top