Connect with us

የፍሳሽ መሰረተ ልማት ውስጥ ባዕድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ተያዙ

የፍሳሽ መሰረተ ልማት ውስጥ ባዕድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ተያዙ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የፍሳሽ መሰረተ ልማት ውስጥ ባዕድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ተያዙ

ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆነው የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፋብሪካ ተረፈ ምርት በቦቴ ተሽከርካሪ በማጓጓዝ እና በባለስልጣኑ የፍሳሽ መስመር ውስጥ በመድፋታቸው ነው፡፡

በተደጋጋሚ በፍሳሽ መሰረተ ልማቱ ላይ የፋብሪካ ፍሳሽ ተረፈ ምርት በመደፋቱ የመዲናዋን ፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በከፍተኛ ወጪ የተገነባው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እና ባዮሎጂካል ክፍሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣኑ ለ24 ሰዓት ክትትል የሚያደርጉ ቡድኖችን በቋቋም ላለፍት 15 ተከታታይ ቀን እና ለሊት ክትትል አድርጓል ፡፡
በዚሁ መሰረት ጥር 24 ቀን 2012 ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በተለምዶ ጠማማው ፎቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባእድ ፍሳሹን በመስመር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ከነተሸከርካሪው በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል፡፡
(የአ/አ ውሀና ፍሳሽ ባለሥልጣን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top