Connect with us

በድጎማ ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ ተሻሻለ

በድጎማ ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ ተሻሻለ
Photo: Facebook

ጤና

በድጎማ ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ ተሻሻለ

የኢትዮጵያ መንግስት ድጎማ በማድረግ ከውጪ እያስገባ ለህብረተሰቡ ሲያሰራጨው የነበረው ፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ መሻሻሉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ፓልም የምግብ ዘይት መንግስት የዋጋ፣ የአቅርቦና የሥርጪት ቁጥጥር እያደረገባቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ከሚቀርቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች አንዱ ነው፡፡

ዘይቱ በውስጡ ካለው የስብ መጠን እና ከአስመጪዎች መረጣ ፍትሐዊነት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችና ውዝግቦችን ለመፍታት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብ ዘይት አቅርቦትና ስርጭት ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 020/2011 አውጥቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

መመሪያው ከታህሳስ/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ከዚህ በኋላ የሚቀርበው ዘይት በፊት ፓልም የምግብ ዘይት ወይም በተለምዶ የሚረጋው ዘይት ሳይሆን ፓልም ኦሊን/palm olien/ የተባለ ፈሳሽ የምግብ ዘይት መሆኑ በመመሪያው ተቀምጧል፡፡

በፊት ይቀርብ የነበረው ፓልም የምግብ ዘይት የጥራት ደረጃ CES138:2015 ተሻሽሎ አሁን የሚቀርበው ፓልም ኦሊን የምግብ ዘይት CES245 የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን አሟልቶ የተመረተና በቫይታሚን ኤ እና ዲ የበለጸገ መሆን እንዳለበትም መመሪያው ያስገድዳል፡፡

ከጥራት ደረጃም መተጨማሪ የዘይት አስመጪዎች ምልመላ፣ የዋጋ ትመና እና የትርፍ ህዳግ ምጣኔ አወሳሰንን የያዘ ሲሆን አቅራቢዎችን ለመመልመል በወጣው መስፈርት መሰረት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ በሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አማካኝነት አሳታፊና ግልፀኝነት ባለው መልኩ 24 የምግብ ዘይት አስመጪዎች ተመርጠው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው የካፒታል መጠን፣ የአስመጪነት ልምድ እና ታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት የዘይት አቅራቢዎች መመልመያ መስፈርቶች ሲሆኑ ውድድሩን አሸንፎ ውል የገባ አስመጭ በገባው ውል መሰረት ሳይፈጽም ቢቀር ከምግብ ዘይት አስመጭነት የሚሰረዝ ይሆናል፡፡

ዘገባው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top