Connect with us

በቻይና የተከሰተውን ቫይረስ ለመግታት መጠነ-ሰፊ የጉዞ እገዳዎች አያስፈልጉም- ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

በቻይና የተከሰተውን ቫይረስ ለመግታት መጠነ-ሰፊ የጉዞ እገዳዎች አያስፈልጉም- ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
Photo: Facebook

ጤና

በቻይና የተከሰተውን ቫይረስ ለመግታት መጠነ-ሰፊ የጉዞ እገዳዎች አያስፈልጉም- ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

በቻይና የተከሰተውን እና እስካሁን ለ426 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ኮሮና ቫይረስ ለመግታት ሲባል በዓለም አቀፍ ጉዞ እና ንግድ ላይ የተደረጉት እገዳዎች አስፈላጊ እንዳልነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ተናገሩ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ “ሁሉም ሀገሮች በማስረጃ ላይ የተመሠረተ እና ወጥነት ያላቸውን ውሳኔዎች እንዲተገብሩ ጥሪ እናቀርባለን” ሲሉ ባለፈው ሳምንት ያስተላለፉትን መልክት ለዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድጋሚ አስታውሰዋል።

ኃላፊው ባለፈው ሳምንት ቫይረሱን በማስመልከት ዓለም አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጁት ወቅትም ይህንኑ መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

ከሀገሪቱ እና ወደ ሀገር በሚደረጉ በረራዎች ላይ ገደብ ከተጣለ እና ሰዎች ከቻይና እንዳይወጡ እገዳዎች በመጣላቸው ምክንያት ቻይና ከዓለም የመገለል ሁኔታዎች አጋጥሟታል።

ዋና ኃላፊው የቫይረሱን ከቻይና ውጭ የመሰራጨት ጉዳይን በተመለከተ ሲናገሩ አነስተኛ እና ስርጭቱም ዘገምተኛ እንደሆነ፣ ነገር ግን ከዚህ በላይ አደገኛ ሊሆን ይችል እንደነበር አስታውቀዋል።

በዓለም ጤና ድርጅት የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የተገኙት የቻይና ልዑካን በበኩላቸው ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባት የሁቤይ ግዛት ፓስፖርትን የያዙ ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የከለከሉ ሀገራት የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም ሲሉ ማውገዛቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።(ኢቢሲ)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top