Connect with us

በአዲስ አበባ ሰባት ህንዳዊያን ህገወጥ መድሃኒት ባዛር ላይ ሲሸጩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዲስ አበባ ሰባት ህንዳዊያን ህገወጥ መድሃኒት ባዛር ላይ ሲሸጩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በአዲስ አበባ ሰባት ህንዳዊያን ህገወጥ መድሃኒት ባዛር ላይ ሲሸጩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሚሊኒየም አዳራሽና መስቀል አደባባይ ኤግዚቢሽን ማዕከል መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ወደ ስምንት ዓይነት የባህላዊ መድኃኒቶች ጸጉርን ለማከምና ለማሳጅ ይረዳል በሚል ደህንነታቸው ፣ ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ በፈሳሽ ቅባትና በዱቄት መልክ የተዘጋጁ ምርቶች በኤግዚቢሽን ማዕከል ባዛር ላይ ሲሸጡ የነበሩ ሰባት የህንድ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

በበድንገተኛ ቁጥጥሩ ወቅት የተያዙት ምርቶችም፦
ካስቱሪር ሄርባል ሄር /KASTURIR HERBALHAIR/
ንላንባሪ ካስቱራ ሄርባል/ NEELAMBARI KASTURA HERBAL/
ንላምባሪ ሄርባል ኦይል /NEELAMBARI, HERBAL OIL/
ካስቱሪ ሄርባል ሄር ኦይል/KASTURI HERBAL HAIR OIL/
ንላምባሪ ሄርባል / NEELAMBARI, HERBAL/
ኤች ኤች አይ ኤን ኬ ኤን አይ /HHINKNI/
ሳንጂቪን ሄርባል አዩስቸር /SNNSEV,N HYREBALE Ayu/
ንላምባሪ ሄርባል ማሳጅ /NEELAMBARI,HERBAL MASSAGE/ የተሰኙ መድሃኒቶች ናቸው።

በተለያየ ስያሜ የተዘጋጁ በፈሳሽ ቅባቶችና ዱቄት መልክ የተዘጋጁ የባህላዊ መድኃኒቶች ባዛሮች ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን ፤መገኘታቸው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡና የማይታወቁ ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀም የባለስልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

በማከፋፈልና በሽያጭ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦች በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ባለስልጣኑ ገልጿል።

የበዓል ሰሞን በመሆኑ ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢዎች ወይም ባዛሮች እንዲሁም የመገበያያ ስፍራዎች ላይ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በማድረግ መሰል ምርቶች ሲያገኝ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ ፣ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንደዲያሳውቁ ጠይቋል፡፡(ኢትዮ ኤፍኤም)

 

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top