Connect with us

የቤኒሻንጉል አንድ ባለሥልጣን በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ

የቤኒሻንጉል አንድ ባለሥልጣን በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የቤኒሻንጉል አንድ ባለሥልጣን በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ

ለመንግስት ሥራ ጉዳይ ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ የነበሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ሰብሳቢ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱላሂ ሶጃር በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አብዱላሂ ሶጃር ዛሬ ጠዋት ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ እያሉ የዳቡስ ወንዝን ተሻግሮ በኦሮሚያ ክልል ቤንጓ አካባቢ በታጣቂዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሠ በየነ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የክልሉ መንግስት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሠቦች፣ ዘመድ ወዳጆች እና መላው የክልሉ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊው ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ዛሬ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ የነበሩት አቶ አብዱላሂ ሶጃር በሸኔ ታጣቂዎች በአሠቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡

በጥቃቱም በመኪናው ውሰጥ የነበሩ 1 ወንድ እና 1 ሴት ላይ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኙም አቶ መለሠ ጠቅሰዋል፡፡

ከክልሉ ተነስቶ አሮሚያ ክልልን የሚያቋርጠው መንገድ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ስጋት የነበረበት በመሆኑን ያታውሱት ኃላፊው፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱን ነው የገለጹት፡፡

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ክልሎች እያከናወኗቸው ባሉ የጋራ የሠላምና የልማት ሥራዎች አንጻራዊ ሠላም ተፈጥሮ እንደነበርም አቶ መለሠ ገልጸዋል፡፡

ክልሎቹ እና ህዝቦቹ ሠላምን ለመስጠበቅ በጋራ እየሠሩ ቢሆንም፣ ታጣቂ ቡድኑ ጫካ ውስጥ መሽጎ በተለይም አመራር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማድረስ ላይ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡ 1 የፖሊስ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸውን ያስታወሱት ኃላፊው፣ የሁለቱን ተጎራባች ክልሎች ሠላም ለማጠናከር የበለጠ እየተሠራ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ጥቃት መፈጸሙ እጅግ የሚያሳዝን ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

“ክስተቱ የሁለቱን ክልል ህዝቦች አይወክልም” ያሉት አቶ መለሠ፣ “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልሎች የጀመሩት የጋራ የሠላምና የልማት ሥራ አጠናክረው ይቀጥላሉ”

ብለዋል፡፡

ሁለቱ ክልሎች ጸረ-ሠላም ኃይሎችን አሁንም በጋራ መታገል እንደሚገባቸው በመጠቆም፣ የፌዴራል መንግስትም ችግሩን ለመፍታት የተለዬ ትኩረት ሠጥቶ ሊሠራ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

የሁለቱ ክልል ህዝቦችም እነዚህን ጸረ-ሠላም ኃይሎች ከህዝብ ለመነጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግስት ጎን በመሆን የደርሻውን መወጣቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡(ምንጭ፡- የቤንሻንጉል ኮምኒኬሽን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top