Connect with us

የገና በዓል ዝግጅት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የገና በዓል ዝግጅት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የገና በዓል ዝግጅት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው የገና በዓል ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅን ለመቀነስና ሲከሰትም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚፈለገውን አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ ከወዲሁ የአቅም ማሻሻያና የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች እየሰሩ ናቸው፡፡ ተደጋጋሚ ችግሮች የሚስተዋልባቸው አካባቢዎችን በመለየት በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጭነት የማመጣጠንና የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

ሆኖም ይህም ተከናውኖ በኤሌክትሪክ መስመሩ ላይ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ሊከሰት ስለሚችል፤ የከፍተኛና የመካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ማለትም የድንጋይ ወፍጮ፣ የፕላስቲክ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የብረታ ብረት፣ የቆዳና ሌዘር፣ የኬሚካልና የመሳሰሉት ፋብሪካዎች፤ ከታህሳስ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6፡00 ድረስ ከግሪድ የሚያገኙትን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳይጠቀሙና መጠቀም ካለባቸውም ሌሎች የኃይል አማራጮችን መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ደንበኞችም በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆን አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ነገሮች አስቀድመው በማዘጋጀት በዋዜማው የሚፈጠረውን የኃይል መጨናነቅን መቀነስ ይችላሉ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዚያት ቢጠቀሙ የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

ኤሌክትሪክ በሚቋረጥበት ጊዜ የጥገና ስራ ለማከናወን የተቋማችንን መታወቂያ የያዙ ባለሞያዎቻችን በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይሁንና የተቋሙ የጥገና ሰራተኞች በመምሰል መሠረተ ልማቱ ላይ ስርቆትና ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አካላት ሊኖሩ ስለሚችሉ፤ ህብረተሰቡ ይህንን ከወዲሁ ተገንዝቦ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮችን በመጠበቅ እንዲተባበር እንጠይቃለን፡፡

ደንበኞቻችን ከኤሌክትሪክ ጋር የተገናኙ መረጃዎች ለመጠየቅ፣ ጥቆማዎችና አስተያይቶች ለማቅረብ ወደ አቅራቢያቸው የሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል መሄድ ወይም 905 ነፃ የጥሪ ማዕከል መጠቀም ይችላሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top