Connect with us

በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ፡፡

በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ፡፡
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ፡፡

በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ፡፡

የገና ጨዋታ መቸ እንደተጀመረ የሚገልፅ ትክክለኛ መረጃ ባይኖርም ከክርስቶስ ልደት በፊት እረኞች በተለይ በበጋው ወቅት ከብት እየጠበቁ መስክ ላይ ይጫወቱት እንደነበር ይነገራል፡፡

ታድያ ይህ ጨዋታ አዝናኝና ተወዳጅ በመሆኑ ዘር፤ የሀብት ደረጃን፤ የሥራ ኀላፊነትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይኖሩት ሁሉንም ሰው ያሳትፋል በዚህም “በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ” እየተባለ ይገጠምለታል፡፡ የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል የሚከበረው የገና ጨዋታ በሚዘወተርበት ወቅት በመሆኑም በዓሉ ሢከበር የገና ጨዋታም በስፋት ይካሄዳል፡፡

ታዲያ በዚህ በዓል ስለ ገና ጨዋታ ጥቂት መረጃ ልናደርሳችሁ ወደናል፡፡ የገና ጨዋታ የኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ፌደሬሽን ጥናት አካሂዶበት ሕግና ደንብ እንደተዘጋጀለት የአማራ ክልል ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን የቀድሞ የሥራ ኃላፊ አቶ ዓለም ሁነኛው ነግረውናል፡፡

የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ከኢትዮጵያ ባህል ማዕከል ጋር በሀገሪቱ 2 መቶ 93 ባህላዊ ስፖርቶች ላይ ጥናት አካሂዶ ነበር፡፡ ለአስራ አንዱ በተካሄደላቸው ጥናት ሕግና ደንብ ወጥቶላቸዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የገና ጨዋታ አንዱ ነው፡፡

በ2006 ዓ.ም ተከልሶ በተዘጋጀው የባህልና ስፖርት ሰነድ መሠረት የገና ጨዋታ ወደ 7 የሚደርሱ ሕግና ደንቦች ተዘጋጂቶለታል፡፡ አቶ ዓለም እንዳብራሩት የተዘጋጀው ሕግና ደንብ የገና ጨዋታ ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በሕግና ደንብ እንዲመራ የሚያደርግ ነው፡፡

የገና ጨዋታ በዓለም ላይ በብዙዎች እንደሚወደደው የእግር ኳስ ጨዋታ የተመልካቾችን ቀልብ የሚስብ አዝናኝ ጨዋታ ነው፡፡ ታዲያ በገና ጨዋታ ደንብ መሠረት የመጫወቻ ሜዳው ምን መሆን እንዳለበት፣ የተጫዋቾች ብዛት፣ የዳኞች ብዛትና ኀላፊነት፣ ውጤት አሰጣጥና ሌሎች አስፈላጊ ደንቦች የተካተቱለት ነው፡፡

ፍጥነትን፤ አካላዊ ጥንካሬንና ትንፋሽን የሚጠይቀው የገና ጨዋታ ሳቢና ተወዳጅ እንዲሆን ልክ እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ደንቦቹ ይመሳሳላሉ፡፡ አቶ ዓለም እንደነገሩን በመጀመሪያ ለገና ጨዋታ ሁለት ተጋጣሚ ቡድኖች ያስፈልጋሉ፤ ለጨዋታ የሚስፈልገው ሜዳም በደንብ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል፡፡

ልክ እንደ እግር ኳስ ሜዳ የጎል ጠባቂ፣ የተከላካይ፣ የአጥቂ፣ የማዕዘን መምቻ በኖራ ይሰመራል፡፡ የሜዳ ስፋቱ ደግሞ ርዝመቱ 90 ሜትር ፤ ጎኑ 50 ሜትር የሆነ ሜዳ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ ሜዳ ውስጥ ለመጫወት ሁለቱ ተጋጣሚ ቡድኖች 15 ተጫዋቾችን ያቀርባሉ፤ አስሩ ሜዳ ውስጥ ገብተው የሚጫወቱ ሲሆን አምስቱ በተቀያሪ ወንበር ይቀመጣሉ፡፡ ጨዋታውን የሚመራ የመሀል ዳኛ፣ ዳኛውን የሚያግዙ መስመር ዳኞች እንዲሁም ተቀያሪ ተጫዋቾችን የሚቀይሩ ዳኞችም የገና ጨዋታ ተሳታፊወች ናቸው፡፡

ታዲያ ገና ጨዋታን ለመጫወት ሩር እየተባለች የምትጠራ ድቡልቡል መጫወቻ ያስፈልጋል፡፡ ክብደቷ እስከ 5 መቶ ግራም የሚመዝን ከእንጨት፤ ከጠፍር አሁን አሁን ደግሞ ከፕላስቲክ ይዘጋጃል፡፡ ድቡልቡል መጫወቻ ወይም ሩሩን ለመምታትና ወደ ተቃራኒ ቡድን ግብ ለማስገባት ልክ እንደ ማንኪያ ቅርፅ ያለው ከ1ሜትር የማይበልጥ ቁመት ያለው የገና ዱላ ያስፈልጋል፡፡ የገና ዱላው ለሁሉም ተጨዋቾች በእኩል ቁመት የተዘጋጀ ሆኖ ይታደላል፡፡

ልዩነት አለመኖሩን ዳኛው የማረጋገጥ ኀላፊነት አለበት፡፡ ጨዋታው ሲጀመር ሁሉም ተጫዋቾች ተነፋነፍ የሚባለውን ባህለዊ ልብሳቸውን ለብሰው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ አጥቂው ከአጥቂ፤ ተከላካይ እዲሁ በቦታው፣ በረኛውም በተጠንቀቅ በቦታው ይሰየማል፡፡

ጨዋታውን የሚያስጀምሩት ዳኛ ሶስት ጊዜ “እዚህ እሩር እዛ ገና ” ካለ በኋላ ጨዋታው ይጀመራል፡፡ በጨዋታው ሕግ መሰረት ሩሯን በእግርና በእጅ መንካት ነጥብ ያስቀንሳል፡፡ ለ30 ደቂቃ በመጀመሪያው ምዕራፍ ይጫወታሉ ለ10 ደቂቃ ረፍት ከወሰዱ በኋላ የጨዋታ ሜዳ ተቀያይረው ሁለተኛ አጋማሽ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

ጨዋታው ለዋንጫ ወይም ለደረጃ ከሆነ ቡድኖቹ ካልተሸናነፉ ተጨማሪ ደቂቃ እንዲጫወቱ ይደረጋል፡፡ በዚህም ካልተሸናነፉ የቅጣት ምት እየተሰጣቸው እስኪሸናነፉ ድረስ ይጫወታሉ፡፡

የገና ጨዋታ አካላዊ ጥናካሬና ፍጥነትን እንዲሁም የብዙ ሰዎች ቀልብ የሚገዛ በመሆኑ ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በሕግና ደንብ መመራቱ አሁን በዓለም ላይ እግር ኳስ የደረሰበትን ተወዳጅነት ያመጣውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በገና ጨዋታ ለማምጣት የሚያግዝ ይሆናል፡፡

የገና ጫዋታን ገና በዓል በሚከበርበት ወቅት ብቻ ከመጫወት ይልቅ ልክ እንደ እግር ኳስ እንዲዘወተር በማድረግ ለዓለም ማስተዋወቅ ስፖርቱ እንዲያድግ ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡ (አብመድ) 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top