Connect with us

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ የሠላም ልዑካን ቡድን ወደኤርትራ ሊያቀና ነው

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ የሠላም ልዑካን ቡድን ወደኤርትራ ሊያቀና ነው

ባህልና ታሪክ

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ የሠላም ልዑካን ቡድን ወደኤርትራ ሊያቀና ነው

ሰለብሪቲ ኤቨንትስ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሕዝቦች ግንኙነት ማዕከል ያደረገ፣ በሁለቱ መንግሥታት መካከል የተጀመረው የሠላም ሒደት የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚስችል “ዳስ ዕርቂ” (የእርቅ ዳስ) የተሰኘ ጉዞ በቅርቡ ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ፡፡
.
የሰለብሪቲ ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ገ/ሊባኖስ እና አቶ ተመስገን ዓለም፣ አቶ ጎይቶም ወልደገሪማ በዛሬው ዕለት በሐርመኒ ሆቴል በጋራ በሰጡት መግለጫ ሰለብሪቲ ባለፉት አራት ዓመታት በመጀመሪያው ምዕራፍ ጉዞው “የሠላም መዝሙር ለኢትዮጽያ እና ለኤርትራ ሕዝቦች” በሚል መሪ ቃል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ በማካሄድ በምሁራን፣ በወጣቶች ፣ በሀገር ሽማግሌዎች ፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በአርቲስቶች፣ በጋዜጠኞች፣ በአክቲቪስቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል ከኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ጋር በመሆን መጠነ ሰፊ ውይይቶችና ምክክሮችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

የዚሁ ዕቅድ አካል በሆነውና በሁለተኛው ምዕራፍ በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረውን ሠላም አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርግ በህወሓት እና በኤርትራው ህግደፍ መካከል እርቀ ሠላም እንዲመጣ የሚያደርግ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ማዕከል ያደረገ ጉዞ ወደኤርትራ በቅርቡ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቀዋል፡፡
.
በዚህ የጉዞ ፕሮግራም ላይ ከሚሳተፉት ከ20 በላይ የልዑካን ቡድን መካከል የእምነት ተቋማት ከፍተኛ መሪዎች፣ አባገዳዎች፣ ታዋቂ ሰዎች እና የመገናኛ ብዙሃን አባላት ይገኙበታል፡፡ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ከኢትዮጽያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እንድሪስ እና ሼህ ቃሲም መሐመድ ታጁዲን፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶሰክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀማዕምራን ፋንታሁን ሙጩ እና አፈመምህር አባ ገብረስላሴ ጌትነት፣ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ፓስተር ጻድቁ አብዶ እና ፓስተር ዘሪሁን ደጉ፣ ከኢትዮጽያ ካቶሊካዊት ቤ/ክ አባ ገብርኤል ወልደሃና እና አባ ጼጥሮስ በርጋ፣ ከኢትዮጵያ ሃይናኖት ተቋማት ጉባዔ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና አቶ ሕሉፍ ወልደስላሴ፣ ከኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት አባገዳ ጎበና ሆላ እሬሶ እና አባገዳ አልዩ መሐመድ ሱሩር እንዲሁም ከተለያዩ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ማለትም ከዋልታ፣ ከሪፖርተር፣ ከኢቢኤስ ቲቪ፣ ከድሬቲዩብ ኦንላይን ሚዲያ፣ ከማትሪክስ የፕሬስ ሥራዎች፣ከቴዲ አብ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት እና የመሳሰሉ በጉዞው ላይ እንደሚሳተፉ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡
.
ጉዞውን የተሳካ ለማድረግ የፈቃድና መሰል ሒደቶች በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የገለጹት አዘጋጆቹ በሁለቱ አገራት መካከል ሕዝብን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ ግንኙነት ለመመስረት የተጀመረው ጥረት በሁሉም ወገኖች በኩል በቀናነት ታይቶ ለልዑካን ቡድኑ አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግላቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top