Connect with us

በሳዑዲ የታገተችው ኢትዮጵያዊቷ ነፃ ወጣች

በሳዑዲ የታገተችው ኢትዮጵያዊቷ ነፃ ወጣች
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በሳዑዲ የታገተችው ኢትዮጵያዊቷ ነፃ ወጣች

በሳዑዲ አረቢያ ከሪያድ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቱማማ የሚባል ሰፈር ሶፍያ እስማኤል በቤት ሠራተኝነት እየሰራች እንዳለች በአሰሪዎቿ ስልኳን ትነጠቃለች፡፡ ከቤተሰብም ሆነ ከማንም ጋር እንዳትገናኝ እንዲሁም ከማድ ቤት ውጭ መውጣት እንዳትችል ትደረጋለች፡፡

በሪያድ የሚኖረው የሶፍያ ባለቤት በአሰሪዎቿ መታገቷን ተረድቶ ወዲያው ወደምትሰራበት ቦታ በማምራት ከአገቷት አሰሪዎች ቤት በመሄድ ለማስለቀቅ የቻለውን ሁሉ ጥረት ቢያደርግም በአሰሪዎቹ ቤተሰቦች በደረሰበት ጥቃት ባለቤቱን ማዳን ሳይችል በመቅረቱ ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ ኤምባሲው ይመጣል።

ኤምባሲው የሶፍያ እስማኤልን መታገትን መረጃ እንደደረሰው ጉዳዩን ይዞ ወደ ሪያድ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታል። ፖሊስ ጣቢያውም አጋች ተብለው የተጠረጠሩትንና ጥቃት አድራሽ የተባሉትን ግለሰቦች ቃላቸውን እንዲስጡ ቢያደርግም፣ ሶፍያን እንዳላገቷትና ከቤት እንደወጣች አለመመለሷን ይገልፃሉ።

የኤምባሲው ዲፕሎማት አቶ ሚስባህ ሙሀመድ አሰሪዎቹ የሰጡት ቃል ከእውነት የራቀ መሆኑን በማስረዳት ፖሊስ ጣቢያው ሶፍያ ከታገተችበት ቤት እንድትወጣና ፍትህ እንድታገኝ ትብብሩን እንዲያደርግ በጠየቁት መሰረት የአሰሪዎቹ ቤት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በፖሊስ እንዲፈተሽ ይወሰናል።

ሆኖም ግን አሰሪዎቹ ቤታቸው በፖሊስ እንደሚፈተሽ ባወቁ ጊዜ ከፍተሻው አንድ ቀን ቀደም ብለው ራሳቸውን ከህግና ከተጠያቂነት ነፃ ለማድርግ እህት ሶፍያን ካገቱበት ቤታቸው ውስጥ በማውጣት ወደ ገበያ ማእከል በመውሰድ እቃ እንድትገዛ በመላክ ጥለዋት ከቦታው ይጠፋሉ።

እህት ሶፍያም ያገቷት ሰዎች ገበያ እንሂድ ብለው ወስደው የጣሏት ከህግ ለማምለጥ እየሞከሩ መሆኑን በመረዳት ወደ ቤተሰቦቿ በመደወል ባለቤቷን አግኝታ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ሪያድ ከተማ የምትገኝ መሆኑን አረጋግጠናል።

የሳዑዲ ፖሊሶች ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ሶፍያ አለችበት የተባለውን ቤት ማለትም የአሰሪዎችን ቤት ለመፈተሽ እና የሰፈሩን ካሜራ ቅጅዎችንና ሌሎችንም መረጃዎች ለመመርመር ወደ ቦታው ቢያመሩም፣ ሶፍያን ሊያገኟት ባለመቻላቸው አሰሪዎቿን እና በባለቤቷ ላይ ድብደባ ያደረሱ ሰዎችን በአሁኑ ሰዓት በህግ ቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።

ፖሊስ የሚያካሂደው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን፣ ኤምባሲው የሶፍያን ጉዳይ ከያዙት ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት በዜጋችን ላይ የመብት ጥሰት ያደረሱ ማለትም እገታና ድብደባ የፈፀሙ ግለሰቦች ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጥረቱንና ክትትሉን የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል።

እህት ሶፍያ እስማኤል በአሁኑ ሰዓት ከእገታው ተርፋ በአሁኑ ሰዓት ከባለቤቷ ጋር በሰላም እና በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia Nebiat Getachew Assegid Spokesperson Office of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top