Connect with us

ሕግ እና ሽምግልና እየተምታታ ይመስላል

ሕግ እና ሽምግልና እየተምታታ ይመስላል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሕግ እና ሽምግልና እየተምታታ ይመስላል

ሕግ እና ሽምግልና እየተምታታ ይመስላል
(ያሬድ ሀይለማርያም)

ሽምግልና እና ሽማግሌ ዋጋ እንዲያጣ ለበርካታ አመታት ብዙ በተሰራበት አገር ዛሬ ለሽምግልና ቅድሚያ መስጠት እና ሽማግሌን ማክበር እጅግ ያስመሰግናል። ይሁንና በሕግ አግባብ ምላሽ ሊያገኙ የሚገባቸውን ነገሮች ሁሉ ለሽምግልን አሳልፎ መስጠት ግን ሌላ የስህተት መስመር ነው። በሽምግልና ስም የወንጀል አድራጎት በተለይም በከፍተኛ ጥፋት ሊያስጠይቁ የሚችሉ ተግባራትን ለፈጸሙ ሰዎች ሽፋን መስጠት የኖርንበትን በጥፋት ያለመጠየቅ ባህልን (culture of impunity) ማስቀጠል ነው።

በቅርቡ ለ86 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ግለሰቦች ምንም እንዳልተፈጠረ ተቆጥሮ በአገራዊ የውይይት መድረኮች ላይ ዋና አጋፋሪ ሆነው ማየት ያለመጠየቅ ከለላ ዛሬም አይን ባወጣ መልኩ መቀጠሉን ነው የሚያሳየው። በቅማንት፣ በጌዲዮ፣ በቡራዩ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በከሚሴ እና በሌሎች ከፍተኛ የሰው እልቂት በደረሰባቸው ሥፍራዎች ለተፈጸሙት አሰቃቂ የወንጀል አድራጎቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው ያለበት የመንግስት አካላት እና ባለሥልጣናት፤ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በስም ተጠቅሰው ተጠያቂ ሲደረጉ እያየን አይደለም።

ይልቅስ በእነዚህ ታዋቂ ግለሰቦች እና የክልል ባለስልጣናት መናጆ ሆኖ የተሳተፉ ወጣቶች ሲዋከቡ እና ሲታሰሩ አይተናል። ይህ በቂ አይደለም። በአገሪቱ እየተንሰራፋ ያለውን ግጭት ለማስቆም ከተፈለገ የድርጊቶቹ ዋና አቀናባሪዎች፣ አነሳሾች፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ባለሥልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች ተጠያቂ ሊደረጉ ይገባል። የፍትህን ጉዳይ በሽምግልና እያለባበሱ መሄድ ግን impunity ከማስፋፋት ባሻገር ያለችንንም ትንሽ ሰላም ያሟጥጥብናል። የሕግ ተጠያቂነትን በሽምግልና እያደባበሱ መሄድ በግፉዋን ደምም መቀለድም ነው።

ፍትሕን ጭዳ እያደረጉ ሆደ ሰፊ፣ ሰላም ወዳድ፣ እርቅ ፈላጊ፣ ሽማግሌ አክባሪ፣ ትዕግስተኛ ወዘተ የመሳሰሉ የሞራል ከፍታ ማሳያዎችን ካባዎች መልበስ መንግስታዊ ባህሪ አይደለም። መንግስት ሕግን የማስከበር፣ ለዜጎች መብጥ ጥበቃ የማድረግ፣ አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረብ እና የማስቀጣት ግዴታ አለበት። እነዚህን አላፊነቱን በየአዳራሹ ሽማግሌዎች ሰብስቦ በማስተቃቀፍ ለመሸፋፈን መሞከር ግን ትልቅ ስህተት ነው።

ፍትሕ ለግፏን! ለሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ ሰዎች ለፍርድ ይቅረቡ!

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top