Connect with us

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የነዳጅ ድርጅት ኀላፊዎች እና ባለሃብቶች ተከሰሱ

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የነዳጅ ድርጅት ኀላፊዎች እና ባለሃብቶች ተከሰሱ

ህግና ስርዓት

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የነዳጅ ድርጅት ኀላፊዎች እና ባለሃብቶች ተከሰሱ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ አቅርቦትና የሽያጭ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አባይነህ አወል እና ሦስት ባለሃብቶች በመመሳጠር በሕዝብ እና በመንግሥት ላይ ከአምስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ ተመሠረተባቸው።

በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 15ኛ ወንጀል ችሎት የተመሠረተው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የድርጅቱ የሥራ ኀላፊዎች ከኤርታሌ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ብሌን ፔትሮሊየም እና ገነት ፔትሮሊየም ጋር ከድርጅቱ አሠራር ውጪ የሆነ ውል በመፈፀማቸው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል።

በድርጅቶቹ ውስጥ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ቴዎድሮስ ተወልደ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ግን ያለመያዛቸውን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

ዐቃቤ ሕግ ታኅሳስ 10/2012 ክሱን ለማሻሻል እና የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ለመስማት በችሎት የቀረበ ሲሆን፣ በክሱ ላይ ገነት ተክለአረጋይ፤ ግርማይ ብርሃነ እና ኤርታሌ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ተዘርዝረዋል።

በክሱ ላይ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የሚሰጠዉን የዱቤ ነዳጅ ግዢ ዉል የድርጅቱ አሠራር በሚጠይቀው መሠረት የውል ማስተማመኛ ዋስትና ድርጅቶቹ ሳያስይዙ ነዳጅ በዱቤ እንዲቀርብላቸው መደረጉ ያልተገባ ጥቅም ለማስገኘት ተብሎ ተፈፅሟል ሲል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ውል ለመፈፀም የሚያስፈልገውን 16 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተለያዩ ዋስትናዎችን ወደ ጎን በማለት ነዳጅ አቅርቧል ሲል ክስ መስርቷል።

የነዳጅ ድርጅቱ ከዉጭ አገር የሚያስገባቸውን የተለያዩ የነዳጅ ምርቶች ለደንበኞቹ በዱቤ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ተቀባይ ድርጅቶቹ ከነዳጅ አቅራቢው ጋር በሚገቡት ዉል መሰረት ክፍያዉን ከፈጸሙ በኋላ አዲስ ውል እንደሚፈፀምላቸው ዐቃቤ ሕግ ጠቅሷል። ተከሳሾች ግን በዱቤ የወሰዱትን ነዳጅ ዋጋ ሳይመልሱ በተደጋጋሚ ነዳጅ እንዲወስዱ ተደርጓል ብሏል።

ከ2010 ጀምሮ የተፈጸሙ የተለያዩ ውሎችን ፖሊስ የመረመረ ሲሆን፣ የድርጅቶቹ ንብረትም ታግዶ እንዳለ አዲስ ማለዳ ማረጋገጥ ችላለች።

የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሙስና አዋጁን መሰረት በማድረግ ሦስት ክሶችን የመሠረተው ዐቃቤ ሕግ፣ በአንደኛ ክስ አምስቱንም ተከሳሾች የጠቀለለ ሲሆን፣ በኹለተኛ ክሱ ላይ የድርጅቱ ሠራተኛ የሆኑትን አባይነህ፣ የድርጅቶቹ ከፍተኛ ባለድርሻ ቴዎድሮስ እንዲሁም ገነትን ከሷል።

የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታደሰ ኃይለማርያምም በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበረ በፌዴራል ፖሊስ እና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያሉ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል። ነገር ግን የማስረጃ ማሰባሰብ ሥራ ባለመጠናቀቁ በዋስትና መፈታታቸውን የገለፁት የአዲስ ማለዳ ምንጮች፣ ድርጅቱ ኦዲት እንዲደረግ መታዘዙንም ጠቅሰዋል። አክለውም በኦዲት ሪፖርቱ መሰረት በዋና ሥራ አስፈፃሚው ላይ ክስ ሊመሰረትም ሆነ ላይመሰረት እንደሚችል ገልፀዋል።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ታደሰ በበኩላቸው ‹‹አልታሰርኩም፣ ኦዲትም ሁልግዜ የሚካሔድ ስለሆነ አዲስ ነገር የለውም›› ብለዋል።

የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተለያዩ የነዳጅ ምርቶችን ከሱዳን ነዳጅ ኮርፖሬሽን፣ ከሳዉዲ አረቢያ እና ከኩዌት በመግዛት በየ15 ቀኑ በሚከፈል ብድር ኢትዮጵያ ላሉ የነዳጅ አከፋፋይ ድርጅቶች ያቀርባል።

ናሽናል ነዳጅ ድርጅት፣ ኮቢል ኢትዮጵያ እና ናይል ነዳጅን ጨምሮ ከ23 በላይ የነዳጅ አከፋፋዮች አሉ። በነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ በኩል በተደጋጋሚ እነዚህ ደንበኞቹ የሚያስይዙት የዋስትና መጠን በዱቤ ከሚወስዱት ነዳጅ ዋጋ እጅግ ያነሰ እና ገንዘቡን ለማስመለስ እንዲሁም ነዳጅ አቅራቢው ከውጪ ነዳጅ የሚያስገባበትን አቅም የሚፈትን እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

(ምንጭ፡-አዲስ ማለዳ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top