Connect with us

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ!!

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ!!
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ!!

በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር የቅበላ መስፈርቶች የማያሟሉ አመልካቾችን እየተማራችሁ ታሟላላችሁ እያሉ የሚከተሉትን መሠረታዊ መስፈርቶች ሳያሟሉ መዝግበው እያስተማሩ እንደሆነ ኤጀንሲው ደርሶበታል፡-

1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የመቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ፣
.
2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅ በሆነ የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ሳያጠናቀቁ ፡-
• የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC level
.
4) ተፈትነው ሳያልፉ፣
• በሙያው ቢያንስ አንድ ዓመት የሥራ ልምድ ሳይኖራቸው እና
.
3. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ሳያለፉ እና በምዝገባው ዕለት ሙሉ ለሙሉ መረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ሳይችሉ ማስተማር በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
.
በተጨማሪም ፡- በ2012ዓ.ም ወደ ግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ የተዘጋጀውን የፍሬሽማን ኮርስ እንዳይወስዱና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚኖራችሁን የ4 ዓመት የቆይታ ጊዜ ወደ 3 ዓመት እንዲያጥርላችሁ እናደርጋለን ብለው ተማሪዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተቋማቸው ገብተው እየተማሩ እንዳሉ በማስመሰል ህገወጥ ተግባር እየፈጸማችሁ የምትገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳላችሁ ለኤጀንሲው ጥቆማ የደረሰ በመሆኑ ይህንን ህገወጥ ተግባር እንድታቆሙ እናሳስባለን፡፡
.
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በወንጀልና በፍትሐብሄር ተጠያቂ እንደሚሆን ኤጀንሲዉ እየገለጸ ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም በጊዜያቸውና በገንዘባቸው ላይ ለሚደርሰው ኪሳራ ኃላፊነቱ የራሳቸውና የተቋሙ ብቻ ስለሚሆን አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳስባል ፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top