Connect with us

ውሀና ፍሳሽ 44 ሚልየን ብር ውዝፍ ክፍያ ከደንበኞቼ ሰበሰብኩኝ አለ

ውሀና ፍሳሽ 44 ሚልየን ብር ውዝፍ ክፍያ ከደንበኞቼ ሰበሰብኩኝ አለ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ውሀና ፍሳሽ 44 ሚልየን ብር ውዝፍ ክፍያ ከደንበኞቼ ሰበሰብኩኝ አለ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ውዝፍ የውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመሰብሰብ ባደረገው ዘመቻ ከ43 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰበ፡፡

ባለሥልጣኑ ገቢውን የሰበሰበው ከ2 ወር በላይ ውዝፍ ዕዳ ካለባቸው ከ38 ሺህ በላይ ደንበኞች ሲሆን የሰበሰበውም በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የቅጣት መክፈያ ጊዜያዊ የክፍያ ጣቢያዎችን በማቋቋም፣ ቅስቀሳ በማድረግ እና አገልግሎቱን በማቋረጥ ነው፡፡

አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ደንበኞች መካከል 14.4 ሚሊየን ብር በላይ ዕዳ ያለባቸው ደንበኞች እስካሁን ቀርበው አልከፈሉም፡፡

ባለሥልጣኑ ውዝፍ ክፍያ ላለባቸው ደንበኞቹ የአገልግሎት የክፍያ ጊዜ በየወሩ ከ26 እስከ 18 መሆኑን አስታውሶ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባቀረበው አማራጮች በመጠቀም በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ደንበኞች ክፍያቸውን የማይፈፅሙ ከሆነ በህግ ለመጠየቅ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

(ምንጭ:- የአ/አ ውሀና ፍሳሽ ባለሥልጣን)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top