Connect with us

ኢዜማ ምርጫውን በብቃት ለማሸነፍ የፋይናንስ ድጋፍ ጠየቀ

ኢዜማ ምርጫውን በብቃት ለማሸነፍ የፋይናንስ ድጋፍ ጠየቀ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢዜማ ምርጫውን በብቃት ለማሸነፍ የፋይናንስ ድጋፍ ጠየቀ

የ #ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) የገቢ እና ሀብት ማሰባሰብ ግብረ ኃይል የፊታችን እሁድ ታኅሳስ 05 ቀን 2012 ዓ.ም የሚያካሄደውን የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ በማስመልከት ዛሬ ታኅሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

ኢዜማ መጪውን ምርጫ በአሸናፊነት መወጣት የሚያስችለውን ሀገራዊ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ ግብረ ኃይል እና ንዑስ ግብረ ኃይሎች አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ በመግለጫው የጠቆመ ሲሆን ከእነዚህ ንዑስ ግብረ ኃይሎች ውስጥ አንዱ የገቢና የሀብት ማሰባሰብ ንዑስ ግብረ ኃይል ዋነኛው መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማሸነፍ እና የኢትዮጵያን ሕዝብ የብዙ ዓመታት የዴሞክራሲ ጥይቄ ለመመለስ ኢዜማ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚገኙ የምርጫ ወረዳዎች ሁሉ መንቀሳቀስ እንዳለበትና ይህንን ለማድረግ ገንዘብ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ ድርጅታዊ ብቃትና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር መተዋወቅና መሥራትን እንደሚጠይቅ የተገለፀ ሲሆን የተጠቀሱትን ሀብቶች ለማሰባሰብም የገቢ እና ሀብት ንዑስ ግብረ ኃይል የመጀመሪያ የሆነውን ዝግጅት የፊታችን እሁድ ታኅሳስ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ እራት ግብዣ የሚያካሄድ መሆኑ ተጠቅሷል።

“መላው ሀገር ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በእራቱ ላይ እንዲታደሙ እና ኢዜማን እንዲደግፉ እንጠይቃለን” ሲል ፓርቲው ጥሪውን አቅርቧል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top