Connect with us

ቤቲ ጂ ስለኦስሎ የሙዚቃ ዝግጅቷ

ቤቲ ጂ ስለኦስሎ የሙዚቃ ዝግጅቷ
Photo: YouTube

መዝናኛ

ቤቲ ጂ ስለኦስሎ የሙዚቃ ዝግጅቷ

#ቤቲ_ጂ_ስለኦስሎ_የሙዚቃ_ዝግጅቷ

<< ጉዳዩ ሰርፕራይዝ እንዲሆን ስለተፈለገ በኔ በኩል ከእናቴና ከእህቴ በስተቀር ማንም አያውቅም ነበር።

ሙዚቃዎቹን ያቀናበረው ያሙሉ ሙሉ እንኳን ከናንተ እኩል በቴሌቭዥን ነው ያየው።

በኋላ እንደተረዳሁት ዶ/ር ዐብይም አያውቁም ነበር።

የኖቤል ኮሚቴው በሚስጥር ከማኔጀሬ እዮብ ጋር ተነጋግረው ነው ዝግጅት የጀመርነው።

ኦስሎ የገባነው ሰኞ ጠዋት ሲሆን ልምምድ የጀመርነውም የዛኑ ዕለት ከሰዓት ነበር።

የፀጉር አሰራሬ ከትግራይ፣ ልብሴ ከአማራ፣ የእጄን ሂና ከሐረሪ፣ ስላደረኩ ዘፈኑ ላይ ደግሞ የኦሮምኛውን “ሲንጃለዳ” ብንጨምርበት “ኢትዮጵያ” ከሚለው ዘፈን ጋር ሁሉንም ያቀፈ ማድረግ ይቻላል ብለን ተነጋግረን የተወሰነ ነው።

ያንን የአሩሲ የአንገት ውዝዋዜ ለሁለት ሳምንት ያህል ተለማምጄ ነው ትንሽ የቻልኩት። የመጀመሪዎቹ ቀናት
ያዞረኝ ነበር ፣ ስትራፖ ሁሉ ያስቸግረኝ ነበር። በሂደት ነው እየቻልኩት የመጣሁት።

እስከዛሬ ከሰራሁባቸው መድረኮች ሁሉ የትላንቱን ለየት እሚያደርገው ንጉስና ንግስት በተገኙበት፣ ጠ/ሚኒስትሩ ባሉበት፣ ፀጥ ብሎ እሚከታተል ታዳሚ ባለበት ሙዚቃ አቅርቤ ስለማላውቅ ደስታም ፍርሃትም ተሰምቶኝ ነበር።

ሽልማቱ ሲያልቅ ከዶ/ር ዐብይ ጋር ተገናኝተን
“በጣም ጎበዝ በርቺ ጥሩ ነው የሰራሽው” ብለውኛል።

ከዝግጅቱ በኋላ ሁለት የኖርዌይ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች
ስለ አልባሳቶቼና ስለ ውዝዋዜዬ ብዙ ጠይቀውኛል።

(ምንጭ፦ ታዲያስ አዲስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top