Connect with us

ለጠ/ሚ ዐብይ ነገ የጀግና አቀባበል ይደረጋል

ለጠ/ሚ ዐብይ ነገ የጀግና አቀባበል ይደረጋል
Photo: Aron Simeneh

ዜና

ለጠ/ሚ ዐብይ ነገ የጀግና አቀባበል ይደረጋል

በትላንትናው ዕለት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የሠላም ኖቤል ሽልማታቸውን የተቀበሉት ጠ;ሚ ዐብይ አሕመድ ነገ ሐሙስ ታህሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ማለዳ አዲስአበባ ሲደርሱ የጀግና አቀባበል እንደሚደረግላቸው ታወቀ፡፡

የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በፌስቡክ ይፋዊ ገጻቸው እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በነገው ዕለት በቦሌ አየር መንገድ አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡

በዚህ የጀግና አቀባበል ፕሮግራም ላይ የከተማችን ነዋሪዎች ቦሌ አየር መንገድ እንዲገኙም ም/ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ባደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል።

በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል።

ሽልማቱም የተሰጠው፦ ጠቅላይ ሚንሥትር ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸውን ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል።


በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ላበረከቱት አስተዋጽዖም በኮሚቴው ተመስግነዋል። ኤርትራ እና ጅቡቲ ሰላም እንዲፈጥሩ ጥረት መደረጉ፤ በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሰላማዊ መፍትኄዎችን እንደ አማራጭ መወሰዳቸው ተወድሷል።
.
«ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት» ያሉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን፤ «የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ] ሀገር ነው፣ በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን» ብለዋል። ኢትዮጵያ በአዉሮጳዉያን ቅኝ አለመገዛትዋ፤ የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ መኾኗ ከመድረኩ ሲገለጥም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ከታዳሚያን ተሰምቷል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top