Connect with us

የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ተገለፀ

የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ተገለፀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ተገለፀ

የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ ቅርሶቻቸው እንደተዘረፉባቸው የየገዳማቱ አስተዳዳሪዎች አስታወቁ፡፡

የኪዳነ ማርያም ብርጊዳ ማርያም ሀመረ ኖህ አንድነት ገዳም አስተዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ኪዳነ ማርያም እንደተናገሩት፤ ገዳሟ በተደጋጋሚ በሌቦች አደጋ ደርሶባታል፡፡ ለዘመናት ጠብቃ ያኖረቻቸው የብራና መፅሐፍትና የተለያዩ ቅርሶች ተዘርፈዋል፡፡

“ለሀገር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ሊሰጡ የሚችሉ የአባቶች ጥበብን የያዙ መፅሐፍት የት እንደደሩሱ አይታወቅም፡፡ በተደጋጋሚ ለመንግስት ብናመለክትም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘንም የሚሉት የገዳሟ አስተዳዳሪ ቅርሶችን ለመታደግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እርብርብ ማድረግ አለበት”ብለዋል፡፡

የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም አስተዳዳሪ መምህር ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ያሳይ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ በጣና ሀይቅ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ገዳማት በጀልባ በታገዙ ሌቦች በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ በርካታ ገዳሞች ቀደም ሲል የተለያዩና ብዙ ቅርሶች ያሏቸው ቢሆንም በአሁን ወቅት በየገዳማቱ የሚገኙ ቅርሶች የተቀበሩ ብቻ ናቸው፡፡

ወደፊት መንግስተ ጥበቃ የማያደርግ ከሆነ በየገዳማቱ የሚገኙ ቅርሶች ሊወድሙ እንደሚችሉ አሳስበዋል፡፡

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መላኩ አላምረው በዚህ ዙሪያ በሰጡ ምላሽ፤ ቅርሶች መዘረፋቸውንና በተደጋጋሚ ለክልሉ መንግስት የድረሱልን ጥሪ መድረሱን አምነው በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዋናነት የዚህ ሁሉ ችግር ክልሉ የባህር ላይ ፖሊስ ያለው አለመሆኑ ነው ያሉት አቶ መላኩ፤ በቀጣይ ይህን መሰል ዝርፊያ ለማስቆም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡

ምንጭ:- ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top