Connect with us

የዱር እንስሳት ማቆያ ማዕከል ለጎብኝዎች ክፍት ሆነ

የዱር እንስሳት ማቆያ ማዕከል ለጎብኝዎች ክፍት ሆነ
Photo: Facebook

ማህበራዊ

የዱር እንስሳት ማቆያ ማዕከል ለጎብኝዎች ክፍት ሆነ

ትሪ-ሃውስ በመባል የሚታወቀው (በሆለታ የሚገኘው ቦርንፍሪ) በእንስሳት ኮቴ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ የሚገኘው የዱር እንስሳት ትምህርት ማዕከል ተገቢውን የዱር እንስሳት ትምህርት መስጠት በሚያስችል ደረጃ ተዘጋጅቶ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል፡፡

የዱር እንስሳት ማቆያ ማዕከል ለጎብኝዎች ክፍት ሆነ

ትሪ-ሃውስ በመባል የሚታወቀው (በሆለታ የሚገኘው ቦርንፍሪ) በእንስሳት ኮቴ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ የሚገኘው የዱር እንስሳት ትምህርት ማዕከል ተገቢውን የዱር እንስሳት ትምህርት መስጠት በሚያስችል ደረጃ ተዘጋጅቶ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል፡፡ ትሪ-ሃውሱ ቀደም ሲል ለስብሰባ አዳራሽነትና ለእንግዶች የካፌ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ማዕከል እንዲሆን በሚያስችል ደረጃ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን እና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማዕከሉ ገልጧል፡፡

ትሪ-ሃውሱ ቀደም ሲል ለስብሰባ አዳራሽነትና ለእንግዶች የካፌ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ማዕከል እንዲሆን በሚያስችል ደረጃ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን እና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማዕከሉ ገልጧል፡፡

ማዕከሉ በተለይም ለዘርፉ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች እና ለህፃናት ከፍተኛ ግልጋሎት እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

የጉብኝት ፕሮግራሞች
ከሁሉም ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚመጡ ቡድኖች፤
• ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ በየሳምንቱ
• መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ 45 ተሳታፊዎች
• ጉብኝቱ የትምህርት ማዕከሉን እና የዱር እንስሳት ማቆያውን ጨምሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 7፡15 ይወስዳል
• ህጻናት እድሜያቸው ከ 7 ዓመት በላይ መሆን ይኖርበታል
• ጉብኝቱ ቅድሚያ ቀጠሮ መያዝ ይኖርበታል

የአካባቢ ኗሪዎች፤
• ቅዳሜ በየሳምንቱ
• ጉብኝቱ የትምህርት ማዕከሉን እና የዱር እንስሳት ማቆያውን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ግማሽ ቀን ድረስ ይወስዳል
• በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ ልጆች በጉብኝቱ መካተት ይችላሉ
• ጉብኝቱ ቅድሚያ ቀጠሮ ማስያዝ አያስፈልግም

አጠቃላይ ጎብኝዎች (የትምህርት ማዕከል ጉብኝት)
• እሁድ በየሳምንቱ
• ከ3፡00 እስከ 10፡30 ድረስ ክፍት ነው፡፡
• ጉብኝቱ የእንስሳት ማቆያ ማዕከሉን አያካትትም
• በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ ልጆች በጉብኝቱ መካተት ይችላሉ
• ጉብኝቱ ቅድሚያ ቀጠሮ ማስያዝ አያስፈልግም

አጠቃላይ ጎብኝዎች (የእንስሳት ማቆያ ጉብኝት)
• እሁድ በየሳምንቱ
• ከ4፡00 እስከ 5፡00 ድረስ ክፍት ነው፤ እያንዳንዱ የጎብኝ ቡድን 10 ሰዎች የሚያካትት ይሆናል (በቅድሚያ ቀጠሮ)
• ከ8፡00 እስከ 9፡00 ድረስ፤ እያንዳንዱ የጎብኝ ቡድን 10 ሰዎች የሚያካትት ይሆናል (በቅድሚያ ቀጠሮ)
• በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ ልጆች በጉብኝቱ መካተት ይችላሉ
• ጉብኝቱ በቅድሚያ ቀጠሮ ማስያዝ ይኖርበታል

ማዕከሉ ዝግ የሚሆንባቸው ቀናት
• ለሁሉም ጎብኝዎች ማዕከሉ ሰኞ እና አርብ በየሳምንቱ ዝግ ነው፡፡(ምንጭ:- የኢት. ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top