Connect with us

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?
Photo: Employment law attorneys

ህግና ስርዓት

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?

የአንድ ግሮሰሪ ኃላፊ ሆነው ሥራ አገኙ እንበል። ያው አዲስ ሥራ እንደመሆኑ መፍራትዎ አይቀርም። ሆኖም አንድ የበላይ አስተዳዳሪ የሥራ ቦታውንና የሥራውን ባህሪ ሊያሳይዎት ወይም ሊያስረዳዎት ፍቃደኝነት ያሳያል።

መጀመሪያ ‘እንዴት ያለ መልካም ሰው ነው?’ ብለው ማሰብዎ አይቀርም። ሆኖም ግለሰቡ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ቢሰጥዎስ? በየሰበቡ ሊዳብስዎ ቢሞክርስ? ምቾት በማይሰጥዎ ሁኔታ ሰውነትዎን ቢነካስ?

ነገሩን ችላ ብለው ሥራዎ ላይ አተኮሩ እንበል። ‘ምናልባትም ችግሩ ከኔ ይሆን?’ ሲሉ ራስዎን እስከመጠራጠር ይደርሳሉ። ቀናት ሲገፉ ግን ‘ምንም አይደለም’ ብለው ቸል ያሉት ነገር ገዝፎ ከቁጥጥርዎ ውጪ ይሆናል።

ይህ ወሲባዊ ትንኮሳ ነው!

ለመሆኑ ወሲባዊ ትንኮሳ ምን ማለት ነው? ምን አይነት ንግግር ወይም ምን አይነት ተግባርስ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ውስጥ ይካተታል?

በሥራ ቦታ ላይ የሥራ ባልደረባን ጀርባ መንተራስ? ስለሥራ ባልደረባ አለባበስ አስተያየት መስጠት? መሳም? የትኛው መስመር ሲታለፍ ነው ይህ ወሲባዊ ትንኮሳ ነው የሚባለው?

ቢቢሲ በተለይም በሥራ ቦታ ላይ የሚደርስ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? በሚል አንድ ማኅበራዊ ጥናት ሠርቶ ነበር። ጥናቱ ምን ያህል ሰዎች ወሲባዊ ትንኮሳ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? የሚል ጥያቄ አጭሯል።

ኬሪ ዊዴት ባሪስታ ናት። “ወሲባዊ ትንኮሳ ምንድን ነው? በሚለው ላይ የግንዛቤ ክፍተት አለ” ትላለች። አብዛኞቹ ወጣት ሴቶችም ይሁን ወንዶች ወሲባዊ ትንኮሳ የሚባለው የትኛው መስመር ሲታለፍ እንደሆነ አያውቁም።

እንደ ሚቱ (#MeToo) እና ታይምስአፕ (#TimesUp) አይነት ንቅናቄዎች፤ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን የሚነቅፉ፣ አጥቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያስችሉም ናቸው። ሆኖም ስንቶች ወሲባዊ ትንኮሳ ምን እንደሆነ ያውቃሉ?

ክብረ ነክ
ወሲባዊ ትንኮሳ ማንኛውም አይነት፣ ያልተፈለገ ወሲብን ያማካለ ንግግር እንዲሁም እንቅስቃሴ ነው። ወሲባዊ ትንኮሳ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ነው። በማንኛውም መንገድ ከክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር ሲከናወን ትንኮሳ ይባላል።

ያልተፈለገ ወሲብ ነክ ድርጊት የደረሰበት ሰው ክብሬ ተነክቷል ወይም አካባቢዬ ምቹ ያልሆነ ስሜት ተፈጥሯል ሲል ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሶበታል ማለት ነው።

የሚያስጨንቅ
አንድ ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ሲደርስበት አስጨናቂ ስሜት ይፈጠራል። አጥቂው ሰው ምን አይነት ስሜት ሊፈጥር አስቦ ተግባሩን ፈጸመ? ከሚለው ስሜት ጋር ፈጽሞ አይገናኝም።

“አንድ ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ለማድረግ ማሰብ ወይም አለማሰቡ ትርጉም የለውም። ወሲባዊ ትንኮሳ ምንጊዜም ወሲባዊ ትንኮሳ ነው።” ስትል ኬሪ ትናገራለች።

Photo: Talent Management & HR

አስቀያሚ ስሜትና ድባብ
ማንም ሰው ምቾት የማይሰጠው ቦታ መሥራት አይሻም። ወሲባዊ ትንኮሳ ደግሞ ምቾት ከሚነሱ አንዱ ነው። አንድ ሰው በወሲብ ነክ በእንቅስቃሴ ወይም በንግግር ደስ የማይል ድባብ ከፈጠረ ትንኮሳ ነው።

አንድ እንቅስቃሴ ወይም ተግባር ወሲባዊ ትንኮሳ ነው ለማለት ከላይ የተዘረዘሩትን ባጠቃላይ መምሰል አያስፈልገውም። ከተጠቀሱት አንዱን እንኳ ከሆነ ወሲባዊ ትንኮሳ ይባላል።

ከሁለት ዓመት በፊት እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት 53 በመቶ ሴቶች እና 20 በመቶ ወንዶች በሥራ ወይም በትምህርት ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሶባቸዋል።

ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች 63 በመቶ የሚሆኑትና 79 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ጥቃት እንደደረሰባቸው ሪፖርት አላደረጉም።

ማንም ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ሊደርስበት ይችላል። ወንድም ሴትም። ወሲባዊ ትንኮሳ ከተቃራኒ ወይም ከተመሰሳሳይ ጾታም ሊሰነዘር ይችላል።

በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ሙከራ ሲደረግ፤ ተጠቂዋ ወይም ተጠቂው፤ ጥቃቱ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጠይቀው ላይቆም ይችላል። ሌሎች ሰዎች ጥቃቱን ቢያዩትም ባያዩትም ወሲባዊ ትንኮሳ ነው።

ብዙ ጊዜ በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲደርስ ሪፖርት ለማድረግ ተጠቂዎቹ እንደሚቸገሩ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።

ኬሬ እንደምትለው “ወሲባዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ሰዎች ለሚያምኑት ወይም ለሚቀርባቸው ሰው ከመናገር መጀመር አለባቸው።” ይህም በመደበኛ ሁኔታ ሪፖርት ለማድረግ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ነው።

የሚሠሩበት ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ፖሊስ፤ ለማን ሪፖርት እንደሚደረግ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት።

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳምን ያካትታል?

• ወሲብ ነክ አስተያየት ወይም ቀልድ

• ሳይፈቀድ መንካት ወይም የንክኪ ሙከራ ማድረግ

• ወሲባዊ መልዕክት ያለው አስተያየት ወይም ዘለግ ላለ ጊዜ በአትኩሮ መመልከት

• መስመር የዘለሉ፣ ወሲባዊ ይዘት ያላችውና የሰውን ግላዊ መረጃ የሚመለከቱ ጥያቄዎች

• ወሲብ ነክ ሀሜቶች ማሰራጨት

• ወሲባዊ ምስል፣ ቪድዮ ወይም ወሲባዊ ይዘት ያለው መረጃ መላክ

Source: BBC Amharic

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top