Connect with us

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 4 ተከሳሾች አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 4 ተከሳሾች አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 4 ተከሳሾች አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው

ተከሳሾች 1ኛ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን 2ኛ ሌ/ኮረኔል ፀጋዬ አንሙት፣ 3ኛ ኮረኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና 4ኛ ኮረኔል መሐመድ ብርሐን ሲሆኑ የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመምራት ከግዢ መመሪያ ውጭ ጥራቱን ያልጠበቀ ራዳር ከ214 ሚሊዩን ብር በላይ በመግዛት በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ በከባድ የሙስና ወንጀል በትናንትናው እለት አዲስ ክስ ተመስርቷል፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች የኢፌዲሪ የብረታብረታና እንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፣ በኮርፖሬሽኑ የሀይቴክ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ የቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ እና እና የኮርፖሬሽኑ የሥነ-ምግባርና የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆኑ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በ2004 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የግዢ መመሪያ አንቀጽ 5.1 መሰረት የግዢ ፈፀሚው አካል ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ጥራት ባለው በተቀላጠፈና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በተወዳዳሪ ዋጋ በጨረታ መፈፀም ሲገባቸው መመሪያውን ወደ ጎን በመተው ያለጨረታ የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የግዢ ፍላጎት ሳይጠይቅ CELEC እና ALIT ከተባሉ የቻይና ኩባንያዎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ራዳሮች ግዢ መፈጸማቸውን ያስረዳል፡፡

የክስ መዝገቡ እንዳመለከተው 2ኛ ተከሳሽ CELEC ከተባለው 101 ራዳሮችን መጋቢት 05 ቀን 2004 ዓ.ም በጠቅላላ የውል ዋጋ 8,581,092.80 የአሜሪካ ዶላር ሞዴል ኤስ ደብሊው አር 6 የጦር መሳሪያ ራዳር ለማቅረብ ውል የተዋዋሉ ሲሆን 3ኛ ተከሳሽ ALIT ከተባለው ኩባንያ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም 10,236,700.00 የአሜሪካ ዶላር 101 ፖርቴብል ሰርቬላንስ ራዳር ለማቅረብ የኢፌዲሪ ብረታብረትና እንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወክሎ ያለአግባብ ውል ተዋውሏል፡፡

4ኛ ተከሳሽ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ እንደመሆኑ መጠን በኮርፖሬሽኑ የግዢ መመሪያ መሰረት ኃላፊዎች የሚወስኗቸውን ውሳኔዎች እና የሚያከናውናቸውን ተግባራት ሕግን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ የሕግ ምክር መስጠትና ውሎች በሕግ አግባብ መከናወናቸውን ማረጋገጥ ሲገባው ከኮርፖሬሽኑ የግዢ መመሪያ ውጪ ያለጨረታና ያለግዢ ፍላጎት 2ኛ ተከሳሽ CELEC ከተባለው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል እንዲጸድቅ ለብኢኮ ዳይሬክተር ለሆነው ለ1ኛ ተከሳሽ ደብዳቤ የጻፈ በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ ውሉን በማጽደቅ በ2ኛ እና በ3ኛ ተከሳሾች በኩል የተፈረሙት ውሎች ጨረታ ሳይደረግ እና የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የግዢ ፍላጎት ሳይጠይቅ የተፈጸ መሆኑን እያወቀ ውሉን ያለአግባብ ያጸደቀ መሆኑን የክስ ዝርዝሩ ይገልጻል፡፡

እንደ ዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዘር የጸደቁት ሁለቱ ውሎች ከALIT ኩባንያ 11 ራዳሮች ከCELEC ኩባንያ 100 ራዳሮች ኢንዱስትሪው የተረከበና ክፍያ የፈጸመ ቢሆንም ለናሙና የመጣ ራዳር በሀገር መከላከያ ሰራዊት በመስክ በተደረገ ሙከራ አገሪቱ ካላት ደረጃ አኳያ ዘመናዊ ያልሆኑ ወጣ ገባ ለሆነ መልዕካ ምድር የማያገለግሉ፣ ስው ፣ እንስሳት እና ሌሎች ግዑዝ ነገሮች የማይለይ፣ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ የሚያስቸግር እና በቀላሉ መጠቀም የማያስችል ሲሆን ከሁሉም ድርጅቶች የተረከባቸውን ራዳሮች እስካሁን ያለአገልግሎት በመጋዘን ውስጥ እንዲከማቹ በማድረግ በአጠቃላይ ለማይጠቅሙ ራዳሮች ግዢ ብር 214,443,021.83 ክፍያ በመፈፀም በህዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ በወንጀል ሕግ አንቀዕ 32 (1/ሀ) እና 411 (1) (ሐ) እና (3) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር በእጃቸው እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ ክሳቸው በችሎቱ የተነበበ ሲሆን የተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ከባድ ስለሆነ ጠበቃ እንደሚያቀርቡ ለፍርድ ቤቱ በመግለጻቸው ለነገ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ጠበቆችን ለማቅረብ ተቀጥሯል፡፡(ምንጭ:-የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top