Connect with us

ክርስቲያን ታደለ እና በለጠ ካሳን ጨምሮ የአብን አመራሮችና አባላት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ

ክርስቲያን ታደለ እና በለጠ ካሳን ጨምሮ የአብን አመራሮችና አባላት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ክርስቲያን ታደለ እና በለጠ ካሳን ጨምሮ የአብን አመራሮችና አባላት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ

ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል አመራሮች እና ከፍተኛ የጦር ጀነራሎች ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትና በሃምሳ አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ስር የቅድመ ክስ ምርመራ ከተከፈተባቸው 13 ተጠርጣሪዎች መካከል የሚከተሉት ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፦

1ኛ) ክርስቲያን ታደለ፤ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ
2ኛ) በለጠ ካሳ፤ የአብን ፅሕፈት ቤት ሓላፊ
3ኛ) አስጠራው ከበደ፤ የአብን አባል
4ኛ) ሲሳይ አልታሰብ፤ የአብን ብሔራዊ ም/ቤት አባል
5ኛ) ፋንታሁን ሞላ፤ የአብን አባል
6ኛ) አማረ ካሴ፤ የአብን የአዲስ አበባ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ
7ኛ) አየለ አስማ፤ የአብን አባል

ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ዐቃቢ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች ለማሰማት የቅድመ ክስ ምርመራ መዝገብ ከከፈተ በኋላ በተሰጠው 3 የጊዜ ቀጠሮ ምስክሮችን ሳያሰማ ክስ ለመመስረት መዝገቡ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይመራልኝ የሚለውን በመቃወም የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት የዋስትና መብት ይከበርልን ጥያቄ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበውን ክስ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።

ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሰረተውን ክስ አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ ሊያስቀጣ የሚችለው ቅጣት ከባድና ዋስትና የማያሰጥ ነው በሚል ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ዐቃቤ ሕግ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ እስኪመሰርት ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ይቆዩ ሲል ውሳኔ መስጠቱን ታውቋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top