Connect with us

በህገ ወጥ መንገድ አለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የሰጠው ግለሰብ ተቀጣ

በህገ ወጥ መንገድ አለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የሰጠው ግለሰብ ተቀጣ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በህገ ወጥ መንገድ አለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የሰጠው ግለሰብ ተቀጣ

ግለሰቡ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተሰጠ ፍቃድ ብቻ ወደ ሀገር ማስገባት እና መጠቀም የሚቻሉት የቴሌኮም መሳሪያዎችን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር በማስገባት ስጠቀም መቆየቱን ፖሊስ ባደረገዉ ምርመራ ደርሶበታል፡፡

የቴሌኮም መሳሪያዎን ወደ ሀገር ለማስገባት፣ ለመጠቀም እና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖረዉ 10 የሚደርሱ ጌት ዌይ የተሰኙ መሳሪያዎች እንዲሁም 30 የሆኑ ቲፒ ሊንክ የተባሉ መሳሪያዎችን ስጠቀም መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ተግባሩም ከዉጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ኢትዮ ቴሌኮም በዘረጋዉ መሰረተ ልማት በኩል ሳይሆን በመሳሪያዎቹ አማካኝነት በዘረጋዉ ኔትወርክ በኩል እንዲያልፉ አድርጓል፡፡

ግለሰቡ ከስልሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ደቂቃ በላይ አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን ማስተላለፉ ታዉቋል፡፡

ከተለያዩ የአለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የተደረጉት ጥሪዎቹ በኢትዮ ቴሌኮም አልፈዉ ቢሆን ኖሮ ኢትዮ ቴሌኮም ያገኝ የነበረዉን ከ321 ሺህ 9 መቶ 96 ብር በላይ እንዲያጣ በማድረጉ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቀርቧል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ግለሰቡ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ለመከላከል የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 761/2004 በመተላለፉ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እና በ 50 ሺህ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣም ወስኖበታል፡፡

(ምንጭ ፌ/ፖሊስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top