Connect with us

በቱርክ በተካሄደው 4ኛው የ2019 ትራቭል ኤክስፖ የኢትዮጵያ ተሳትፎ የተሳካ እንደነበር ተገለጸ

በቱርክ በተካሄደው 4ኛው የ2019 ትራቭል ኤክስፖ የኢትዮጵያ ተሳትፎ የተሳካ እንደነበር ተገለጸ

ባህልና ታሪክ

በቱርክ በተካሄደው 4ኛው የ2019 ትራቭል ኤክስፖ የኢትዮጵያ ተሳትፎ የተሳካ እንደነበር ተገለጸ

ከህዳር 4 እስከ 7 ቀን 2012 ዓም በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ የተካሄደው የተካሄደው አራተኛው የ2019 ትራቭል ኤክስፖ የኢትዮጵያ ተሳትፎ የተሳካ እንደነበር ተገልጿል።

በዝግጅቱ በቱርክ አንካራ ከተማ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የአገራችንን የታሪክ፣ ባህል እና ሃይማኖታዊ ቅርሶች፣ የቡና አፈላል እና የብሔር ብሔረሰቦችን የባህል ውዝዋዜ በማሳየት ሰፊ የአገር ገጽታ ግንባታ እና የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል። በዚህም የኢትዮጵያ ተሳትፎ የተሳከ እንደነበር ከጎብኝዎቹና ከተሳታፊዎቹ ተገልጿል።

በማዕከሉ በአገራችን የተዘጋጀው ማሳያ በቱርክ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ በአንካራ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎች ተጎብኝቷል።

 

የአገራችን የቡና አፈላል እና ባህላዊ ጭፈራ በታዋቂው የቱርክ ሚዲያ አናዶሉ ኤጀንሲን ጨምሮ በሌሎች የዜና አውታሮች ሰፊ ሽፋን አግኝቷል ሲል መረጃውን ያደረሰን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ነው፡፡

ህዳር 09 ቀን 2012 ዓ.ም

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top