Connect with us

በኦሮሚያ 540 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ 540 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ህግና ስርዓት

በኦሮሚያ 540 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የነበረው የፀጥታ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቶ መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል።

ሰሞኑን በክልሉ በተፈጠረው የሰላምና የጸጥታ ችግር ውስጥ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት ውስጥ በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማና በፀጥታ አካላት ብርቱ ክትትል ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኝ ሲሆን ችግሩ ከተከሰተበት ቀን አንስቶ እስከ አሁን 540 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እስከ አሁን በክልሉ የህግ የበላይነት ለማስፈን በተሰራው ስራ ውስጥ ኅብረተሰቡ ያደረገና እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለኅብረተሰቡ ታላቅ ምስጋና አቅርቧል።

በተመሳሳይ ኮሚሽኑ የተለያዩ የወንጀል ድርጊት ፈፅመው ለጊዜው ከአካባቢው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎች ይዞ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋልና በክልሉ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ለማስቀጠል እንዲቻል የተለመደው የኅብረተሰቡ መረጃ የመስጠት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

(የመረጃ ምንጭ፣- የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ማህበራዊ ሚዲያ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top