Connect with us

ቋራ በጀግናው መንፈስ ደመቀች

ቋራ በጀግናው መንፈስ ደመቀች

ባህልና ታሪክ

ቋራ በጀግናው መንፈስ ደመቀች

ቋራ በጀግናው መንፈስ ደመቀች፤ አንድ ህልም ብናጣም፤ አንድ ህልም ያሳየንን መሪ የሚያከብር ትውልድ ዛሬም አለ፡፡ 

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ትናንት በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ በድምቀት የተመረቀውን የዳግማዊ ቴዎድሮስ ሐውልት አስመልክቶ ቋራ በጀግናው መንፈስ ደመቀች ይለናል በተከታዩ ዘገባው፡፡) ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
_
ቋራ አይደለሁም፤ ቋራ መኾን ግን ተመኝቼ ነበር፡፡ ገለጉ ስትሞሸር መቅረት ያስቆጫል፡፡ አደባባይዋ ጀግናን ለመዘከር የመይሳው ሐውልት ቆመበት፡፡ እርግጥ ነው አሁን አንድ ህልም አጥተናል፡፡ አንድ ህልም አሳየን ብለን ጀግናውን በመናፈቅ የምንዘፍን ትውልድ ኾነናል፡፡ ህልም አልባ እንዳልኾንን ማሳያዋ ግን ቋራ ነች፡፡ አንድ ህልም የሚናፍቅን ጀግና በክብር ዘክራዋለችና፤ ከአልጣሽ ወንዝ ወዲህ ከገለጉ ወንዝ ማዶ ከጀግኖቹ መታሰቢያ ተራሮች መለስ ስሟ በህያው ታሪክ ከተጻፈው ደጋዋ የቴዎድሮስ ከተማ በታች በቋረኞቹ መዲና አንዱን ሰንበት አንድ ታሪክ ተሰራ፡፡

እያንዳንዱ የደግ ልብ ባለቤት ቋራ ገብቶ ዓይኑ የሚንከራተተው የአባ ታጠቅን ፊት ፍለጋ ነበር፡፡ ቋረኞች አደረጉት፡፡ ዛሬ ገለጉ የደረሰ የዓይኑ ማረፊያ ቆሞ ይመለከታል፡፡ ይህ ቅርስ ሲመረቅ አለመኖር ይቆጫል፡፡ ወዳጆቼ ነገሩኝ፤ እርግጥ አስቀኑኝ ይበልጥ ይገልጸዋል፡፡

እዚያ የኾነውን ሰምቶ አለመኖር የማይነግስበት መንፈስ የለም፡፡ ብቀርም መንፈሴ አለ፡፡ አንድ ህልም የምታይ ሀገር ዜጋ መኾን ስለምፈልግ አንድ ስለመኾን ልቡም ክንዱም የደከሙትን ጀግና እወደዋለሁ፡፡ ለምትወደው ጀግና ሐውልት የምታቆም ሀገር ለትውልድ ቅርስ እየተወች ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ገለጉ መይሳውን አትተርከውም ከሚደመጥ ወደሚታይ መታሰቢያ ቀይራዋለች፡፡

በዚህ ሐውልት ባሻገር ከዳር የተነሳ መንፈስ መካከሉን እንደምን እንደፈወሰው ትውልድ ይማራል፡፡ የገለጉ ጎዳና መንገድ ብቻ ሳይሆን መድረሻም ይኾናል፡፡ ወደ አንድነታችን መድረሻ፣ ወደ አባቶቻችን ክብር መድረሻ፣ ወደ ተከበረች ኢትዮጵያ መድረሻ፡፡ ሐውልቱን እያየ የሚያድግ ትውልድ አንገት መድፋትን ይጠየፋል፡፡ ስለ ሀገር ክብር ይማራል፤ የሚያነድ ክንድ ባለቤት መሆንን ስለሚሻ ክንዱም መንፈሱም አይማረክም፡፡ እንዲህ ባለው መንፈስ ለመጠመቅ እስክመጣ ገለጉ ናፍቃኛለች፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top