Connect with us

ማንነት እና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የሚያነሳሱና የሚፈጽሙ አካላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል-ኢዜማ

ማንነት እና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የሚያነሳሱና የሚፈጽሙ አካላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል-ኢዜማ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ማንነት እና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የሚያነሳሱና የሚፈጽሙ አካላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል-ኢዜማ

በሀገሪቱ ዜጎች ላይ ማንነት እና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የሚፈጽሙና የሚያነሳሱ አካላት ለህግ ሊቀርቡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ አሳሰበ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ከተመሠረተ ጀምሮ ያከናወናቸውን እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በፓርቲውን አጠቃላይ ሀገራዊ እይታ ዙሪያ ገለፃ አድርጓል።

በዚህም ኢዜማ በመላው ኢትዮጵያ 400 በሚጠጉ የምርጫ ወረዳዎች አባላትን ማደራጀት መቻሉን እና በ214ቱ የራሳቸው ጽሕፈት ቤት ከፍተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን በማደራጀት 32 የድጋፍ ማህበር መቋቋሙን እንዲሁም በ16 ዘርፎች ለአማራጭ ፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ የጥናት ውጤቶች መዘጋጀታቸውም ተነግሯል።

በሌላ በኩል በሀገሪቱ ባለፉት 27 ዓመታት ማንነት ላይ ተመስርቶ የተገነባው የፖለቲካ ስርዓት በሃይማኖት ተቋማት እና የዕምነቱ ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲደርስ በማድረግ የዜጎችን ህይወት እያስቀጠፈ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

ይህም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ላለው የለውጥ ሂደት እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ችግሩን በፍጥነት ለመቅረፍም መንግስት ማንነት እና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የሚፈጽሙና የሚያነሳሱ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባው አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈም በደረሱ ጥቃቶች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ማድረግ እና የተጀመሩ የሕግ እና የተቋማትን መልሶ የማቋቋም ስራዎች በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።(ምንጭ:-ፋና)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top