Connect with us

ከ«ኢስላሙማ ፊ ኦሮሙማ» ጋር የተዋወቅኹበት ዕለት

ከ«ኢስላሙማ ፊ ኦሮሙማ» ጋር የተዋወቅኹበት ዕለት
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ከ«ኢስላሙማ ፊ ኦሮሙማ» ጋር የተዋወቅኹበት ዕለት

ከ«ኢስላሙማ ፊ ኦሮሙማ» ጋር የተዋወቅኹበት ዕለት
———
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)

ማስገንዘቢያ እና አቋም
——–
ይህንን ጽሑፍ ከማቅረቤ አስቀድሜ የአቋም መግለጫ መሰል ሐሳብ ለማቅረብ እገደዳለኹ። ይህም በኋላ ስም በማጥፋት ላይ የሚጠመዱ ሰዎች ሌላውንም እንዳይበክሉ ጤነኛውን ወገን ቀድሞ ለማሳሰብ ያህል ነው።

1ኛ. ኢትዮጵያ የብዙ ብሔረሰቦች እና የብዙ እምነቶች ሀገር እንጂ የአንድ ብሔረሰብ/ ቋንቋ እና የአንድ እምነት ብቻ አይደለችም ብዬ አምናለኹ፣

2ኛ. አሁን በሀገራችን ላይ መከራውን ጸናው አክራሪ ብሔርተኛ እና አክራሪ ሙስሊም ብዙውን የኦሮሞ ሕዝብ እና ብዙውን ሙስሊም አይወክሉም ብዬ አምናለኹ፣

3ኛ. በተለየ የምወደውና ልሞትለት ወይም ልገድልለት የምፈልገው ብሔር/ብሔረሰብ/ሕዝብ የለኝም፣

4ኛ. በብሔርተኝነት ከተቆጠረብኝ በአጥንት ደም ሥሬ ውስጥ እንደ አፋሩ የኢርታ-አሌ እሳት የሚንቀለቀል ኢትዮጵያዊነት ነው ያለብኝ፣

ሐተታ፡-
—–
ጊዜው ገና ወታደራዊ መንግሥት በነበረበት ዘመን ነበር። ገና በልጅነት ዕድሜዬ፣ ስለ ሀገሬ የተጻፉ መጻሕፍትን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ጥርግርግ አድርጌ በማነብባቸው ዘመናት በአንዱ ቀን ለረዥም ዘመን «በኦነግነት እና በኦሮሞ መብት ታጋይነት» በእስር ቤት ሲማቅቅ የኖረ አንድ አዛውንት ዘመዴ ከእስር ቤት ተለቅቆ ሊጎበኘን መጣ። አረጋዊ ነው። እግሩ በሕመምና በጤና መጓደል ያስነክሰዋል። «ሪህ አለችብኝ» ብሎናል በኋላ ላይ ከልጅነት ወንድሜና አብሮ አደጌ ከግርማ ወ/ሩፋኤል ጋር ሆነን ሲያወጋን።

ሽማግሌ ቢሆንም ከእኛ ከለጋ ወጣቶቹ ጋር ቀላል የማይባል ደስ የሚል ጊዜ ነበር ያሳለፈው። ስለ ብዙ ነገር ተወያይተናል። ገና High School እንኳን በቅጡ ያልጨረሱ ልጆች ናቸው ብሎ ሳይንቀን በታሪክ፣ በፖለቲካና በእስር ቤት ሕይወት ዙሪያ ብዙ አጫውቶናል። ከእነዚያ ንግግሮች ሁሉ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ በሕሊናዬ የቀረችውን አንዲት ታሪክ ላጫውታችሁ።

«አፋን ኢስላማ» (የእስልምና ቋንቋ)
———
ይህ ዘመዴ ስለ እስር ቤት ሕይወት ሲያጫውተን፣ በመንግሥቱ ኃ/ማርያም እስር ቤቶቹ የታሰሩ ብዙ ኦሮሞዎች መኖራቸውን፣ ለምን እንደታሠሩ ከነገረን በኋላ «አንዳንድ ኦሮሞዎች እንዲህ ብለው ይጠይቁኻል። አፋን ኢስላማ ቤክታ ይሉኻል። የእስልምና ቋንቋ ትናገራለህ ማለታቸው ነው። የእስልምና ቋንቋ የሚሉት አረብኛውን እንዳይመስልህ። ኦሮምኛውን ነው። ኦሮሞ ሁሉ ሙስሊም ነው ወይም ሙስሊም መሆን አለበት ብለው ያምናሉ» አለኝ። ገረመኝ። ያቺ ታሪክ በልጅነት ልቤ ሰሌዳ ላይ ተጽፋ ቀረች። እናም የሰሞኑ የኦሮሚያ ጭፍጨፋ እና የሐረርጌ ዕልቂት ዓይነት ታሪክ ስሰማ የዚያ የዘመዴ ታሪክ ትዝ ይለኛል። በርግጥም ኦሮሞ ሆኖ ክርስቲያን መሆን፣ ኦሮሞ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ መሆን አይቻልም የሚል ቡድን እንዳለ ይኸው በእሳትና በሜንጫ እያስተማረን ነው። ጉድ በል ሸዋ!!!!!!

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top