Connect with us

ህዳር ሠርግ አለባችሁ፤ ኑና የ700 ዓመቷን ሙሽራ ደብረ ሲናን እንሞሽራት፤

ህዳር ሠርግ አለባችሁ፤ ኑና የ700 ዓመቷን ሙሽራ ደብረ ሲናን እንሞሽራት፤

ባህልና ታሪክ

ህዳር ሠርግ አለባችሁ፤ ኑና የ700 ዓመቷን ሙሽራ ደብረ ሲናን እንሞሽራት፤

ህዳር ሠርግ አለባችሁ፤ ኑና የ700 ዓመቷን ሙሽራ ደብረ ሲናን እንሞሽራት፤

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በያዝነው ዓመት ከተመሰረተች 700 ዓመት የሆናትን ደብረ ሲና ማርያም ገዳም ኑና እንሞሽራት ሲል በተከታዩ ዘገባው ስለ ታሪካዊቷ ገዳም ይነግረናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬቲዮብ

የጣና ዳር ጌጥ ናት፡፡ ዘመን ተሻጋሪ መገለጫችን፡፡ ደግሞ የትስስር ገመድ ናት፡፡ ጣናን ከስሜን ሸዋ ደብረ ሲና ጋር አጋምዳለች፡፡ ገዳም ስትሆን ጥበብ ለመቶ ዓመታት አኑራለች፡፡ አእዋፍ ሀገራቸው ደጃፏ ነው፡፡ ለጎርጎራና አካባቢው ኩራት ሆና ኖራለች፡፡ ኢትዮጵያን ብለው ጣና የደረሱ ሳይረግጧት አያልፉም፡፡

በወርሃ ህዳር የዛሬ 700 ዓመት ተመሰረተች፡፡ ብዙ ዘመን ኖራም ዛሬ ወጣት ናት፡፡ ወጣት ሆና ያላየችው ታሪክ የሌለ የማንነታችን መገለጫ፡፡ ደብረ ሲና የእምነት ስፍራ አይደለችም፡፡ ወደ ኋላ ወስዳ የኪነ ህንጻ ጥበባችንን ብቃት ታስታውሰናለች፡፡ በሳር እንደምን አድርገን ቆርቆሮ እንሰራ የነበርን የተፈጥሮ መሃንዲሶች እንደነበርን ምስክር ናት፡፡

ህዳር 21 ደብረ ሲና 700 ዓመቷን በድምቀት ታከብራለች፡፡ ጎርጎራ ዳግም ደብረ ሲናን በማርያም ንግስ ትድራለች፡፡ ሙሽራዋ ደብረ ሲና ሰርጓን ጠርታለች፡፡ በውሃ ለሚጓዙ ከባህር ዳር ብዙ ተአምር አይተው የሚደርሱባት ድንቅ ስፍራ ናት፡፡ በየብስ ለሚመጣውም እንዲሁ ዙሪያዋን የሀገር ቅርስ ከቧታል፡፡

700 መቶ አመት መኖር ቀላል አይደለም፡፡ 700 ተአምር አላት፡፡ የግድግዳ ስዕሎቿ የአባቶቻችንን ጥበብ የሚመሰክሩ እማኞች ናቸው፡፡ ደንቢያ እንኳን ከብት ሰው ማልመድ መቻሉን የመጣ ይመሰክራል፡፡ የጎርጎራ ውበትና የደብረ ሲና ልደት እኩል የገጠመበት ህዳር ጣና ዳር መሆንን የመሰለ ነገር የለም፡፡

በእውቁ የፊልም ሰው በፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ጤዛ ፊልም የምትመለከቷት ቤተ ክርስቲያን ደብረ ሲና ናት፡፡ ክቧ የሳር ክዳን የለበሰች ድንቅ ቅርስ፡፡ ስትደምቅ ባንዲራ ትለብሳለች፡፡ ደብረ ሲናን እንዲህ ሆና ማየት መታደል ነው፡፡ አልታደልኩም የሚል እንዲህ ስትዋብ ያላየ ነው፡፡

ደብረ ሲና ነበርኩ ያለ አንድ አፍታ ማንዳባን ያያል፤ ጀበራ ማርያም ቅርብ ናት፡፡ የአጼ ሱሲንዮስ ቤተ መንግስት እዚያው አለ፡፡ ደግሞ እነ አንጋረ ተክለሃይማኖትና ደሴተ ጊዮርጊስን ማየት መታደል ነው፡፡ ደብረ ሲና ስትሞሸር መኖር ለዚህ ሁሉ በረከት መብቃት ነው፡፡ አእዋፍ የሚያዜሙባት ቀደምት ቅርስ 700 ዓመት ያስቆጠረች የኢትዮጵያ ሀብት ናት፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top