Connect with us

የኦሮሚያ ክልል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ችግር የተሳተፉ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠየቀ

የኦሮሚያ ክልል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ችግር የተሳተፉ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠየቀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኦሮሚያ ክልል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ችግር የተሳተፉ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠየቀ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንደሚያወግዝና በዚህ ድርጊት የተሳተፉ አካላትን ከፌዴራል መንግስትና ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ለሕግ እንደሚያቀርባቸው ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃ በዩኒቨርቲው በተማሪዎች ላይ በተፈጸመው ድርጊት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱን የገለጹት ም/ፕሬዝዳንቱ በርካታ ተማሪዎች ላይም ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡

የጥፋት ኃይሎች ዓላማ ሰላም እንዳይኖር በማድረግ እና ህዝቡን ስሜት ውስጥ በማስገባት የህዝቦችን አብሮነት ማፍረስ፣ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መተማመን እንዳይኖር ማድረግ መሆኑን ህዝቡ ተረድቶ፣ ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ ሁኔታ ነገሮችን ማየት አለበት ብለዋል፡፡

“ህዝባችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር በሰላም በመኖር ታላቅነቱን ማስመስከር አለበት” ብለዋል አቶ ሽመልስ፡፡

ም/ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ከሌሎች ክልሎች የመጡና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ መስራት እንዳለበትና ተማሪዎቹን እንደ ልጆቹ እንክብካቤ አድርጎላቸው የጥፋት ኃይሎችን ፍላጎት ማክሸፍ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቶ ሽመልስ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስም በሁለቱ ተማሪዎች ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top