Connect with us

እንባዎት ትዕቢተኛውን ትውልድ ሳይኾን የትዕቢተኛውን ትውልድ እኩይ ሀሳብ ጠራርጎ ይውሰድልን!!

እንባዎት ትዕቢተኛውን ትውልድ ሳይኾን የትዕቢተኛውን ትውልድ እኩይ ሀሳብ ጠራርጎ ይውሰድልን!!
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

እንባዎት ትዕቢተኛውን ትውልድ ሳይኾን የትዕቢተኛውን ትውልድ እኩይ ሀሳብ ጠራርጎ ይውሰድልን!!

እንባዎት ትዕቢተኛውን ትውልድ ሳይኾን የትዕቢተኛውን ትውልድ እኩይ ሀሳብ ጠራርጎ ይውሰድልን!!
እንደ እርስዎ ያሉ አባቶች ዛሬም ” እባክህ ልጆች ናቸው” ብለው ከፈጣሪ እየተሟገቱልን ነው፡፡
ሄኖክ ስዩም በድሬቲዮብ

ቀዳሚ ሙፍቲ ከሸገር ጨዋታ ጋር የነበራቸው ቆይታ የእረፍት ቀናቱ አጀንዳ ነበር፡፡ ከሁሉም አብልጦ ልቤን የጎዳኝ እንቅልፍ ያሳጣኋቸው ትውልድ አባል መኾኔ ነው፡፡ ዋርካዎቻችን ወደ ጥላው አልሰበሰብ ብለን የጭንቅ ሕይወት ይመራሉ፡፡ ከርዕዮት ዓለም ፋሽን ወደ መገዳደል ገብተን ስለ እኛ ለሚማጸኑ አባቶች የእንባ ምክንያቶች ኾነናል፡፡

እዚህ ሀገር የአባት ስራው ማልቀስ ነው፡፡ ትናንት በከፋ ጦርነት፣ በስደትና በመከራ አባት አልቅሷል፡፡ አባት ስለልጆቹ የሚያለቅስበት ምክንያት የኾነ ትውልድ ተተክቷል፡፡ በአባቶቹ እንባ እየዋኘ ዓለሙን የሚቀጭ ትውልድ አባል በመኾኔ እድለኛ አይደለሁም፡፡

ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር የኢትዮጵያ ጉዳይ ስቃይ ኾኖባቸዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ የሚያዩትን በተረት እንኳን አልሰሙትም፡፡ እናም ስለ ኢትዮጵያ ያለቅሳሉ፡፡ የሚያስለቅሰው ትውልድ ከአስለቃሽ ጭስ ቢያርፍም ከማስለቀስ አልታቀበም፡፡

የሚሰማው ያስለቅሳል፡፡ የምሽቱ ማጠቃለያ ዜና የሰው መሞት፣ የሰው መሰደድ፣ ሰው መሰቃየት ነው፡፡ ይኼንን ሰምቶ እንደምን ያለ ቅን ልብ እንቅልፍ ይወስደዋል? ይልቁንስ እርስ በእርስ እረፍት አጥቶ አባቶቹን እረፍት ያሳጣ ትውልድ እስከመቼ በጥፋት ጎዳናው ይከንፋል የሚለውን ሳስብ እፈራለሁ፡፡

እንባ ፍርሐትን ያስወግዳል፡፡ አባቶች እንባ ስለ ኢትዮጵያ ሲወርድ ሳይ ፈጣሪ ምህረት ስለማድረጉ አስባለሁ፡፡ ልቡን እንደ ፈርዖን ያደነደነ ትውልድ ያለ ቅጣት አይመለስም ብሎ ካሰበስ እልና መልሼ ደግሞ እሰጋለሁ፡፡ ልቡ የደነደነ ትውልድ ደህና በትር ካላረፈበት እንደምን አደብ ይገዛል? መለስ እልና በወንድም ከመሞትና ወንድምን ከመግደል በላይ በትርስ ከወዴት አለ እላለሁ፡፡ በዚህ መካከል ስለ ኢትዮጵያና ስለ እኔ ትውልድ ለሚያነቡ አባቶች መንታ ስሜት ይሰማኛል፡፡

እውነት ነው ከአንድ ትልቅ አባት የሚጠበቀውን አድርገዋል፡፡ ፈጣሪን እየሆነ ስላለው ነገር ለምነውታል፡፡ ድንገት ከተኙበት ተነስተው ስለ ትውልዱና ስለሚያስፈራው ድባብ ያነባሉ፡፡ የእንባም ጡር አለው፡፡ ይኽ እንባዎት የኔን ትውልድ ጠርጎ እንዳይኼድ እፈራለሁ፡፡ እንደ እርስዎ ያሉ አባቶች በያሉበት እያለቀሱ ነው፡፡ መሪር ለቅሶ እንደ ራሄል ራማ ይሰማል፡፡ የለቅሶችሁ ምክንያት ይኽ ትውልድ ነው፡፡ በዘር የሚባላው ትውልድ፤ እናም ፈጣሪ እንዳይቀጣው ፈራሁ፡፡

እንባችሁ ለምህረት ይሁንልን፡፡ እንባችሁ ክፋትን ከምድራችን ይጥረግልን፡፡ ከእንባችሁ የተነሳ ትውልዱ ልብ የነገሰው ዘረኝነት ይታጠብ፡፡ ከእንባችሁ የተነሳ በኔ ትውልድ የገነነው የሞት መንፈስ ይጠረግ፡፡ ክፉ ነገራችን ሁሉ በተጠራቀመችው የጠብታ እንባችሁ ታጥቦ አዲስ መንፈስ በሀገሬ ይታይ፤

ልብ የሚጎዳ እውነት ነው፡፡ ለሚበላላ ትውልድ ከማልቀስ በላይ መፍትሔ የለም፡፡ መጠፋፋት ለሚሻ ተተኪ ከፈጣሪ ጋር ማውራት ብቻ ነው መፍትሔው፡፡ ትውልድ ሲያሳጣን አባት አልነሳንም፡፡ እንደ እርስዎ ያሉ አባቶች ዛሬም ” እባክህ ልጆች ናቸው” ብለው ከፈጣሪ እየተሟገቱልን ነው፡፡ ፈጣሪ ይኼንን ይስማችሁ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top