Connect with us

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በግጭቱ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ አረጋገጠ

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በግጭቱ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ አረጋገጠ
Photo: Tiksa Negeri/Reuters

ህግና ስርዓት

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በግጭቱ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ አረጋገጠ

– ከ400 በላይ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል፣ ዋና የግጭቱ ጠንሳሾች በተመለከተ ግን የተሰጠ መረጃ የለም፣

በኦሮሚያ ክልል በቅርቡ በተከሰተው ግጭት እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ የክልሉ መንግስት ገለጸ። በግጭቱ ከ400 ባይ ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን የግጭቱ ዋና ጠንሳሾችና ስምሪት ሰጪዎች ለመያዝ ሀሳብ ስለመኖሩ በዘገባው በቀጥታ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ በቀጥታ ለክልሉ ተጠሪ በሆኑ 19 ዋና ዋና ከተሞች ላይ በተካሄደው የሠላም ኮንፈራንስ የህዝቡ አቋም በግጭቱ እጁ ያለበት አካል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን የሚል ነው። የክልሉ መንግስትም ከህዝብ የተለየ አቋም የለውምና ይህን ፍላጎት ይተገብራል።

‹‹ህዝብ የተስማማበት ይፈፅማል።›› ያሉት ኃላፊው፣ ከ400 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ይህም ተግባር ተጠናሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።በጉዳዩ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ አቶ ዴሬሳ ገለፃ፤በየቦታው የተፈጠረው የሰላም ችግር የየትኛውም ህዝብ ፍላት አይደለም። በመሆኑም ህዝቡ አቋም ላይ የደረሰው እንዲህ አይነቱን የሰላም ችግር በጋራ ሆኖ ለመመከት ነው።ግጭቱ ኪሳራ ነው ያስከተለው በመሆኑም ህዝቡ አይደግፈውም። ድርጊቱን በፅናት እንደሚታገለውም አቋም መያዙን አስታውቋል።

ህዝቡ የሚፈልገውም በጋራ ሰላሙን ማስጠበቅ ነው።ፍላጎቱም የኦሮሞ ህዝብም አቃፊነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው።ግጭቱ የኦሮሞ ህዝብን አይገልጽም፤ የኦሮሞ ህዝብ ከብሄር ብሄረሰቦችም ጋር በተለመደው መልኩ አብሮ መኖር እንደሚፈልግ በውይይቱ ወቅትም አረጋግጧል።

የሰላም ኮንፈራንሱ ይዘትም የክልሉን ሰላም በማስፈን የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እንቀስቃሴዎችን ለማሳለጥ ፣ሰላምንና የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ያጠነጠነ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህ እንቅስቃሴ ደግሞ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።ኮንፈረንሱም በዚህ ስራ ውስጥ ከህዝቡ የሚጠበቀውን ድርሻ ሊወጣ በሚችልበት አግባብ ላይ የተካሄደ መሆኑን አብራርተዋል።

እንደ ምክትል ቢሮ ሃላፊው ገለጻ፤በውይይቱም መግባባት ላይ ተደርሷል።ህዝቡም ከመንግስት ጋር ሆኖ ማናቸውንም ሰላማዊ እንቅስቃሴን የሚያወኩ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ሚናውን መወጣት ይኖርበታል።

ከመንግስት ጎን እንዲቆምና ወንጀለኞችን እንዲያጋልጥም ይጠበቃል።ይህም የክልሉን ሰላምና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ በጋራ ለመስራት ያስችላል።ሁሉም በየአካባቢው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የበኩሉን መወጣትና ትኩረቱንም ወደ ልማት መመለስ ይኖርበታል።

‹‹ግጭቱ ህዝቡንም ሆነ ወጣቱን የሚመለከት አይደለም›› ያሉት ምክትል ኃላፊው ፣ታዲያ ማንን ነው የሚመለከት ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ ‹‹ህዝቡ ጥያቄውን ለማቅረብ በወጣበት ጊዜ ጉዳዩ የኃይማኖትና የብሄር መልክ እንዲይዝ ለማድረግ ያደረጉ አካላትን ነው የሚመለከተውን›› ብለዋል።ቤተ ክርስቲያን ሊያቃጥል እንዲሁም መስጂድ ሊያፈርስ ሲሯሯጥ የነበረው አካል ኃይማኖተኛ ሳይሆን የፖለቲካ ነጋዴ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሠላም ኮንፍረንሱ ላይ በክልሉ ያሉ ሁሉም ብሄር እና ብሄረሰብ የተሳተፈበት ሲሆን፣ወጣቶችን፣ሴቶችን፣አዛውንቶችን፣ የኃይማኖት አባቶችንና ሌሎችንም ማካተቱ ታውቋል።ኮንፈረንሱ ወደ ቀበሌ በመውረድ የሚካሄድ እንደሆነም ይጠበቃል።

(ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ጥቅምት 25/2012)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top