Connect with us

ከ- ስንሞት ኢትዮጵያ ወደ ስንሞት ብሔር ብሔረሰብ

ከ- ስንሞት ኢትዮጵያ ወደ ስንሞት ብሔር ብሔረሰብ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ከ- ስንሞት ኢትዮጵያ ወደ ስንሞት ብሔር ብሔረሰብ

ከ- ስንሞት ኢትዮጵያ ወደ ስንሞት ብሔር ብሔረሰብ
(በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን)

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በፓርላማ ሲሰየሙና ንግግር ሲያደርጉ የብዙዎችን ቀልብ ከያዘው ንግግራቸው ውስጥ የአንድን አዛውንት አባባል ጠቅሰው፣‹‹ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን›› ሲሉ የተናገሩት ነገር አንዱ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ትናንት ማታ በሰጡት መግለጫ ላይ ሟችን በብሔራቸው ዘርዝረዋል፡፡ሃይማኖታቸውንም ገልፀዋል፡፡ብሔሩ ያልተረጋገጠውን ሟች ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› ብለው አልፈውታል፡፡

እጅግ ያሳዝናል፡፡ሰዎች ሰው ሆነን መኖር ከጀመርን በኋላ የሟቾች አስከሬን በብሄር ሲከፋፈል በርግጥም ልብ ይሰብራል፡፡‹‹ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ›› ብለው ልባችንን ያሞቁት ጠቅላይሚኒስትር ዛሬ መጥተው ሟቾችን በብሔር ሲያከፋፍሉን በርግጥም አሳፋሪ ነው፡፡

በርግጥ ጥቃቱ ብሔር ተኮር መሆኑ ሀቅ ነው፡፡የእርስበርስ ግጭት በብሔርና በሃይማኖት እንደሚቀሰቀስ ጥርጥር የለውም፡፡ባለፉት ዓመታት ያልሞተበት ብሔር የለም፡፡የትናንቱን የጠቅላይሚኒስትሩን መግለጫ የተመለከቱ ሰዎች እንኳን ለድሬቱዩብ በላኩት መልዕክት ‹‹በደብረ ዘይት ከተማ 7 ሰውዎች ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህ ዉስጥ 2 ወላይታዎች ለምን ተረሱ። ነገርዮው በብሔር ከሆነ ለምን እነዚህስ አይጠቀሱም ነበር›› ብለዋል፡፡

እንዲህ ያለ ጣጣ ነው የሚያመጣው፡፡ሁሉን ነገር የመቆጣጠር ሥልጣን ያለው መንግሥት ሟቾቹን ከሞት መጠበቅ ሲገባው ሟቾቹን በብሔር አከፋፍሎን ዘወር አለ፡፡

ከዚህ ክስተት ካልተማርን ከምንም ምን እንማር… እንጃ! በትናንቱ መግለጫ ቢያንስ ሁለት ነገር መማር አለብን፡፡በአንድ በኩል መንግሥት የአስከሬን አሀዝ በብሔር ከማደል ውጭ እዚህ ግባ የሚባል ሚና እንደማይኖረው፣በሌላ በኩል ደግሞ የመንግሥትን አቅመ ቢስነት ተረድተን ኢትዮጵያዊያን በትብብር ሠላማችንን ለማስፈን እንድንተጋ ነው፡፡

ይህ በርግጥም ኢትዮጵያዊያን ከምንም በላይ በጣም ፈጥነን ሠላም የምናሰፍንበት ሁኔታ ላይ እንድንረባረብ የሚያደርገን ነው፡፡እንደዛ ካልሆነ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንደምንሆን የገለፀልን መንግሥት ስንሞት ብሔር ብሔረሰብ እንደምንሆን ትናንት ባየነው መግለጫ ተገንዝበናል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top