Connect with us

ሚኒስትር ዲኤታውም እንደኔ ማማረር ጀመሩ

ሚኒስትር ዲኤታውም እንደኔ ማማረር ጀመሩ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሚኒስትር ዲኤታውም እንደኔ ማማረር ጀመሩ

ሚኒስትር ዲኤታውም እንደኔ ማማረር ጀመሩ
(በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን)

መቼም ዘንድሮ ነገሩ ሁሉ ተዘበረራርቆብናል፡፡መሪው ከተመሪው እኩል ያለቅሳል፤ ይበሳጫል፡፡ መፍትሔ መፈለግ ሲገባው ከምዕመኑ እኩል ያማርራል፡፡ በውነቱ ግራ አጋቢ ነው፡፡ መንግሥት በምድራችን ላይ ትልቁ ስብስብና ጠንካራው ኃይል ነው፡፡መንግሥት የተቋማት ጥምረትና ሕብረት ውጤት ነው፡፡የጥንካሬውም ምንጭም ይሔው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የመንግሥትን ተቋማት የሚመሩ ሹመኞች፣ ከእኛ እኩል ሆድ እየበሳቸው ነው፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በትግራይና አማራ ፖለቲከኞች መሀል የተፈጠረ መቃቃር በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩትን ካሳ ተ/ብርሃንን አስለቀሰ፡፡ ከዚያን ወዲህ ደግሞ ሠላም ያመጡልናል፣ አገር ይጠብቁልናል ያልናቸው የሠላም ሚኒስትሯ ከአንድም ሁለቴ ተንሰቅስቀው አለቀሱ፡፡ አጃኢብ ነው፡፡

አሁን ደግሞ የሠላም ሚኒስቴር ዲኤታ ልክ እንደተራው ዜጋ፣ ልክ እንደ አልፎሂያጅ ሰው፣ ልክ እንደ አሉባልተኛ አክቲቪስት ሲያማርሩ አየሁ፡፡ ዶ/ር ስዩም መስፍን ናቸው፡፡ የሠላም ሚኒስትር ዲኤታ ብቻ ሳይሆኑ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልም ናቸው፡፡
እኒህ ትልቅ ባለሥልጣን፣ እኒህ ሹመኛ፣ እኒህ የዩኒቭርሲቲ መምህር (የነበሩ) ሰው የፃፉት መልዕክት የሚከተለው ነው፡፡

“አሁን ጃዋርና ግብርአበሮቹ በህግ ባልተጠየቁበት ሀገርና ሁኔታ ስለ ህግ ማስከበር/መከበር ማንም ግለሰብ/የመንግስት ተቋም የመናገር ሞራል የለውም። በህግ የሚያስጠይቀው ቢያንስ ደግሞ ከሀገር የሚያስባርረው ብዙ ማስረጃዎች ያሉበት ወንጀለኛ በህግ አለመጠየቅ ፤ የአያሌ ንጽሀን ደም እንዲያፈስ ከመፍቀድ አይተናነስም።

እሱ ቆሞ እየሄደ፣ እንደፈለገው እየፈነጨ አቃቤ ህግ ሌሎችን የመክሰስ የማሰር የሞራልም የህግም ልእልና የለውም!!!! ግዜው አጠረም ረዘመም በህግ መጠየቁ ግን አይቀርም!!!!!!!”

እዚህ ጋር ነጥብ ላንሳ! እንግዲህ የኢትዮ መንግሥት ምክርቤትን ከመሠረቱት ተቋማት አንዱ ሠላም ሚኒስቴር ነው፡፡ ይህ ተቋም የአገሪቱ ሥራ አስፈፃሚ ምክርቤት አባል ነው፡፡ ለዚያውም በውስጡ ፌደራል ፖሊስን፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነትንና መሠል የፀጥታ ተቋማትን ይዞ ነው-የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የሆነው፡፡

ይህንን ሁሉ ነገር ማድረግ የሚችለው (መሠለል፣መመርመርና ማሰር) የሠላም ሚኒስቴር ውስጥ የሚሠሩት ምክትል ሚኒስትር ግን ልክ እንደኛ እንደተራው ዜጋ ‹‹እሱ ቆሞ እየሄደ፣ እንደፈለገው እየፈነጨ አቃቤ ህግ ሌሎችን የመክሰስ የማሰር የሞራልም የህግም ልእልና የለውም!!!! ግዜው አጠረም ረዘመም በህግ መጠየቁ ግን አይቀርም›› እያሉ ይዝታሉ፤  ይበሳጫሉ፡፡

እኒህ ሰው ከእኛ የተሻለ ነገሮችን ወደ ሕጋዊ መስመር ለማስገባት እድሉ አላቸው፡፡ አንደኛ በራሳቸው ሚኒስቴር አጀንዳው ተይዞ ወደ ሚኒስትሮች ምክርቤት መምጣት ይችላል፡፡ ፖሊስና ደኅንነት በስሩ ስላለ ይህንንም ተጠቅሞ ወደ ሚኒስትሮች ምክርቤት ሳይሄድ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህ ካልሆነም ቢያንስ በእርሳቸው እናት ድርጅት አዴፓ በኩል ነገርዮው አጀንዳ ሆኖ ወደ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲሄድ ግፊት ማሳደር ይችሉ ነበር፡፡

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top