Connect with us

ኢሀን ‹‹የሽግግር መንግሥት›› እንዲመሰረት ጠየቀ

ኢሀን ‹‹የሽግግር መንግሥት›› እንዲመሰረት ጠየቀ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢሀን ‹‹የሽግግር መንግሥት›› እንዲመሰረት ጠየቀ

የኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሀን) የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት በድጋሜ ጠየቀ፡፡ ንቅናቄው የሽግግር መንግሥት ይዋቀር ጥያቄውን በይፋ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡

ኢሀን ከሰሞነኛው ጥቃትና ግጭት ጋር በተያያዘ በሰጠው መግለጫ፤ አሁን ላይ መንግሥት አለ ብሎ ለማመን እንደሚከብደው ተናግሯል፡፡

ምክንያቱን ሲያስረዳም ስርዓት አልበኝነት ሰፍኖ፣ ዜጎች ኢ-ሰብኣዊ ድርጊቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

የኢሀን ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት የፀጥታ አካላት ባሉበት አገር እንዲህ መሆኑም መንግሥት ትንሹ ግዴታው የሆነውን የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ ያለመቻሉ ማረጋገጫ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በመሆኑም መፍትሔው የሽግግር መንግሥት መመስረት እንደሆነ ንቅናቄው ያምናል ተብሏል፡፡

ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ሲመጡ በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም ጭምር ስለሽግግር መንግሥት መቋቋም ተጠይቀው ‹‹እኔ አሻግራችኋለሁ›› በማለት ጥያቄውን ማጣጣላቸው አይዘነጋም፡፡

(ምንጭ፡-አሐዱ ቴሌቪዥን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top