Connect with us

የትግራይ ክልል መግለጫ ምን ያህል ታስቦበታል?

የትግራይ ክልል መግለጫ ምን ያህል ታስቦበታል?
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የትግራይ ክልል መግለጫ ምን ያህል ታስቦበታል?

የትግራይ ክልል መግለጫ ምን ያህል ታስቦበታል? | በጥሩሰው አዲስ

ያሳፍነው አመት ለሀገራችን እጅግ በርካታ አስቸጋሪ ጊዜያቶችን አሳይቶ ያለፈ አመት መሆኑ የምንዘነጋው አይደለም ፡፡ይፈጠሩ የነበሩት የፖለቲካ አለመረጋጋቶች የፈጠሩት ስጋት እስካሁን ዘልቋል ህዝቡንም እርስበእርስ እንዲፈራራና እንዳይተማመን አድርገውታል፡፡ ከነዚህ አለመረጋጋቶች ውስጥ በዩኒቨርስቲዎቻችን ውስጥ የተፈጠሩት የዘር እና የማንነት ተኮር ፀቦች ለብዙዎች ንፁሀን ተማሪዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆነዋል፡፡

ይህም ሁኔታ የኢትዮጵያውያንን ልብ የሰበረ ነበር ፡፡ይህንን ሁኔታ ከግምት በማስገባት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስደንጋጭ እና አሳዛኝ መግለጫ አውጥቷል ይህም የትግራይ ክልል ትምህር ቢሮ ወደ አማራ ክልል አዲስ ተማሪዎችን እንደማይልክ ማስታወቁ ነበር፡፡

እንደ ቢቢሲ አማርኛ ዘገባ ከሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ”ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ወደ ሚሰነዘሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እና ኃላፊነት ወደማይወስድ ክልል አዲስ ተማሪዎችን አይልክም እንግዲህ ይህ መግለጫ ልዩነቶቻችን እና መከፋፈላችን ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሱ የሚያሳዩ ይመስለኛል ፡፡

በእርግጥ አለመግባባቶች እና ዘር ተኮር ግጭቶች እስከ ህይወት መጥፋት ድረስ የበርካቶችን ህይወት አሳጥቶናል ታዲያ ይህ ሲሆን ይህንን ጉዳት ያደረሰብንን የመከፋፈል እና እንደጠላት የመተያት አባዜ አንድነታችንን በማጠንከር ከሚያለያዩን ሀሳቦች ይልቅ ይበልጥ የሚያቀራርቡንና የሚያዋህዱንን ሃሳቦች በማምጣት መዋጋ ስንችል የወደፊቷን ኢትዮጲያን የሚረከቡ ወጣቶች ከክላቸው ውጪ እንዳያስቡ እና እንዳያውቁ አድርጎ አጥብቦ ማሳደግ ተገቢ አይደለም ተማሪዎች በክልላቸው ውስጥ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተክታትለው ሲያበቁ ወደሌሎች ክልሎች ለትምህርት ተመድበው ይሄዳሉ ታዲያ በዚህ ወቅት ከትምህርታቸው እኩል የሚሄዱበትን ክልል ባህል ወግ አኗኗር አብረው ከሚማሩ ከሌሎች ቦታዎች ከሚመጡ ወጣቶች ኢትዮጲያዊነትን ጭምር ተምረው ይመለሳሉ፡፡

ይህንን እውነት ማንኛውም ዩኒቨርስቲ ገብቶ የወጣ ኢትዮጲያዊ የሚያውቀው ነው፡፡ የትግራይ ክልላዊ መግለጫ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከግምት በማስገባት ቢታረም መልካም ነው፡፡ለክልሉ መግለጫ ምላሽ የሰጠው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ክሉ የህንን የማለት ስልጣን እንደሌለው ገልፃል፡፡ የትግራይ ክልል መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው ዘንድሮ በአማራ ክልል ወደሚገኙ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ከ2ሺህ በላይ እንደነበሩና ከሚመለከተው አካላት ጋር በተደረገው ንግግር ቁጥሩ ወደ 600 ዝቅ እንዲል መደረጉን ተገልጿል። በዩኒቨርስቲዎቻችን በርካታ የትግራይ ክልል ተማሪዎች በአሁኑ ሰአት እየተማሩ ይገኛሉ፡፡

የአዲሶች ተማሪዎች መቅረት ለጉዳዩ መፍትሄ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሰላም እንዲኖር ሁሉም በትብብር ቢሰራ የተሻለ መፍትሄ የሚያመጣ አካሄድ ነው ፡፡ከዚህም ባለፈ ተማሪዎች እራሳቸው እሄዳለሁ ወይም አልሄድም ብለው መወሰን ሲችሉ አልክም ብሎ በክልል ደረጃ ውሳኔ መስጠት በተማሪዎች ስነልቦና ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ የወደፊቱን የወጣቶቻችንን አብነትም ከድጡ ወደማጡ የሚያወርድ አካሄድ ነው፡፡ መሪዎቻችን ምን ጊዜ ውሳኔ ከማሳፋቸው በፊት ውሳኔያቸው በሀገርና ዜጎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለማሳደሩን ልብ ሊሉ ይገባል ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top