Connect with us

ከ1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሰረቁ ሶስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ከ1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሰረቁ ሶስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ
አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ህግና ስርዓት

ከ1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሰረቁ ሶስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ከ1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ከመኪና ውስጥ የሰረቁ ሶስት ተጠርጣሪዎች በሕብረተሰቡ እና በፖሊስ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡

ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ/ም የሚንግ ሲያ ስትሮንግ ማሽነሪ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ የግል ማህበር ባለቤት ሚስተር ፒን ላፊ ላንግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከሚገኘው አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥተው በኮድ 2 B 23934 አ.አ ቪትዝ መኪና ገንዘቡን አስቀምጠው ለምሳ ወደ ሆቴል ቤት በገቡበት ወቅት ሶስቱ ግለሰቦችበኮድ 2 B 01156 አ.አ ቪትዝ መኪና የግል ተበዳይን በመከታተል የመኪናውን መስታወት በመስበር ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ይዘው ለማምለጥ ሙከራሲ ያደርጉ ተይዘዋል፡፡

በአካባቢው ሲንቀሰቀሱ የነበሩት ዋ/ሳጅን ዳዊት ካሳሁን ፣ ም/ሳጅን ሀብታሙ ጎበዛይ እና ሌሎች ግለሰቦች ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪዎቹን ፣ ገንዘቡ እና ተሽከርካሪውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ሩዋንዳ በተለምዶ ጉሊት ገበያ አካባቢ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን ተረፈ ይጥና ገልፀዋል፡፡

በህብረተሰቡ እና በፖሊስ አባላት ትብብር ተጠርጣሪዎቹ ተይዘው ገንዘባቸው በመመለሱ ሚስተር ፒን ላፊ ላንግ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ወንጀል ፈፃሚዎቹን ለመያዝ የፖሊስ አባላቱና ግለሰቦቹ ያደረጉትን እንቅስቃሴ ማድነቃቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top