Connect with us

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ተሰብሮ ታሸገ

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ተሰብሮ ታሸገ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ተሰብሮ ታሸገ

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ተሰብሮ ታሸገ

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

የአዲስአበባ የዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተርና የስነአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም ደራሲ የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኘው ፅ/ቤታቸው ትላንት እሁድ ከቀኑ 5:00 ሰአት ገደማ የበር ቁልፉ ተሰብሮና ተቀይሮ መታሸጉ ተሰማ።

የአይን እማኞች ለድሬቲዩብ እንደገለፁት በእረፍት ቀን የዶክተር ዳዊትን ቢሮ ሰብረው የገቡት የጥበቃ ሰራተኞች ባነጋገሯቸው ወቅት ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር የታዘዙበት ደብዳቤ ማሳየታቸውን ጠቁመዋል። በር እንዲሰበር ያዘዘው አካል በህጋዊ መንገድ ደብዳቤ ለዶክተር ዳዊት በመፃፍ የሚፈልገውን መፈፀም እየቻለ ለምን ከእሳቸው እውቅና ውጪ በር ሰብሮ ቁልፍ ቀይሮ ቢሮ እንዲታሸግ እንዳደረገ ምክንያቱ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

የዚህ እርምጃ ምክንያቱ በግልፅ ባይነገርም ከሰሞኑ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ዳዊት አንድ ለአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ኘረዝደንት ቅርብ ነው የተባለ ግለሰብ በተደጋጋሚ አስፈራርቶኛል በማለት ችግሩ እንዲታረም ለዩኒቨርሲቲው ኘረዝደንት የፃፉት ደብዳቤ ሾልኮ በማህበራዊ ድረገፃች ከመውጣቱ ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ዶ/ር ዳዊት ከፍተኛ ተነባቢነት ያገኘው “አለመኖር” የተሰኘ መፅሐፍ ደራሲም ናቸው።

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል በጉዳዩ ላይ ያለውን አስተያየት ለማካተት በስልክ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። እንደተሳካ ምላሻቸውን እናቀርባለን።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top