Connect with us

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ለዕድለኛ ደንበኞቹ  አስረከበ 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ለዕድለኛ ደንበኞቹ አስረከበ
Bunna international Bank s.c

ማህበራዊ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ለዕድለኛ ደንበኞቹ  አስረከበ 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ለዕድለኛ ደንበኞቹ  አስረከበ 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ላለፉት ወራት ሲያካሂድ የቆየውን የሰባተኛውን  ዙር የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ ይሸለሙ ፕሮግራም እና የአራተኛውን ዙር የታክሲና ባጃጅ የሹፌሮችና ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ዕጣ ለወጣላቸው ደንበኞቹ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

ባንኩ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ባካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ በሁለቱም ፕሮግራሞች የእጣ አሸናፊዎች ለሆኑት ባለእድሎች የአውቶሞቢሎች፣ የባጃጆች፣ የስማርት ቴሌቪዠኖች፣ የስማርት ስልኮች እና ዲኤስቲቪ ዲኮደሮች ሽልማት አበርክቷል።

ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሪ በቡና ባንክ ቅርንጫፎች በኩል ሲቀበሉና ሲመነዝሩ የሽልማት ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን የዕጣ ኩፖኖች የሚቀበሉበት አሰራር የዘረጋው ቡና ባንክ ባለፉት ወራት ባካሄዳቸው ስድስት ዙሮች የዕጣ ኩፖኖችን በማዘጋጀት በባንኩ በኩል የውጭ ምንዛሪ የሚቀበሉና የሚመነዝሩ ደንበኞቹን ሲሸልም ቆይቷል።

የዛሬው ሽልማት የ7ኛው ዙር የይቀበሉ ይሸለሙ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ሲሆን ሲሆን የዕጣ ባለእድል ለሆኑት ደንበኞቹም  ለአንደኛ ዕጣ ሱዙኪ የቤት አውቶሞቢል ፣ለሁለተኛ ዕጣ አምስት ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች፣ ሶስተኛ ዕጣ አምስት ስማርት ሞባይል ቀፎዎች እና አራተኛ ዕጣ አምስት የሳተላይት ዲኮደሮችን  ለባለእድሎች አዘጋጅቶ አስረክቧል።

ይኸው የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ ይሸለሙ መርሃ ግብር በህጋዊ መንገድ የሚካሄድ የውጭ ምንዛሪ ለውጥን በማበረታታት ሃገሪቱ ልታገኝ የምትችለውን ጥቅም በማረጋገጥ ረገድ አይነተኛ ድርሻ እንዳለው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ያምናል።

በተመሳሳይም ባንኩ የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የየዕለት ቁጠባ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩና ነገ ያሰቡበት ራዕይ ላይ እንዲደርሱ የተመቻቸ “የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ቁጠባ አገልግሎት”  በማዘጋጀት ብዙዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።

በቋሚነት በባንካችን በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የየዕለት ገቢ ያላቸውን የታክሲና የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የቁጠባ ባህል ለማሳደግ ነገን ከወዲሁ እንዲሰሩት የሚያስችል እድል ተከፍቶ ለአራት ተከታታይ ዙሮች ተጠቃሚዎችን በስፋት ለማካተት የሚያሰችሉ ተግባራት ተከናውነዋል።

ይህንን አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ለማበረታታትም ባንኩ የዕጣ ኩፖኖችን በማዘጋጀት ላለፉት ሶስት ዙሮች የተለያዩ ዓይነት ሽልማቶችን አዘጋጅቶ ለእድለኞች አስረክቧል። በዛሬው አራተኛው ዙር ማጠናቀቂያ ፕሮግራምም በተመሳሳይ እጣ ለወጣላቸው እድለኞች ሱዙኪ የቤት አውቶሞቢል፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችና ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ሸልሟል።  

የሁለቱም አገልግሎቶች ቀጣይ ዙር በቅርቡ ተጀምሮ በሂደት ላይ በመሆኑ ደንበኞች የአገልግሎቱም የማበረታቻ ዕጣውም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባንካችን በዚህ አጋጣሚ ይጋብዛል።

ባንኩ ወደፊትም መሰል የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል የሚያሳድጉና የውጭ ምንዛሪ ህጋዊ ዝውውርን የሚያበረታቱ የሽልማት ፕሮግራሞችን በተከታታይ ዙሮች እያዘጋጀ የተለመደ ቀልጣፋ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ማዳረሱን ይቀጥላል።

ከተመሰረተ 11 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በከፈታቸው 249 ቅርንጫፎቹ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top