Connect with us

የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ የአፈፃፀም ደረጃ ተገመገመ 

የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ የአፈፃፀም ደረጃ ተገመገመ
የኢፌደሪ ስፖርት ኮሚሽን

ስፖርት

የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ የአፈፃፀም ደረጃ ተገመገመ 

የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ የአፈፃፀም ደረጃ ተገመገመ 

ግምገማው የተካሄደው በኮሚሽኑ ፣በግንባታ ተቋራጩ እና በአማካሪ ድርጅቱ መካከል ሲሆን ፕሮጀክቱ የደረሰበት ደረጃ ፣በግንባታ ሂደት በአጋጣሙ ችግሮች እና በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎችን ያካተተ ሪፖርት ቀርቦ ሰሞኑን ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በተለይም ለግንባታ ፕሮጀክቱ በቂ የሰው ሀይል ከማሰመራት ፣አስፈላጊውን የግንባታ ማሽነሪ ከማስገባት እና በስራ እቅድ ከመመራት አኳያ የግንባታ ተቋራጩ ተገምግሟል ፡፡

ግምገማውን የመሩት የኢፌደሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡርአቶ ዱቤ ጅ ሎ እንዳሉት የሰው ሀይል እና አስፈላጊው የግንባታ ቁሳቁስ እና ማሽነሪ በአልተሟበት ሁኔታ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰው ተቋራጭ ድርጅቱ በፍጥነት አስፈላጊውን የሰው ሀይል እና የስራ ግብዓት በመሟላት ግንባታውን ሊያፋጥን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ፡፡

ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጅ መሳሪያዎችን በተያዘለት ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደሚገባ እና አሁን እየተካሄደ ከሚገኘው ግንባታ ጎን ለጎን ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎች በማቀናጀት ግንባታውን ማፋጠን ይገባል ሲሉም አቶ ዱቤ አሳስበዋል ፡፡

በኮሚሽኑ እና በመንግስት በኩል ሊፈቱ የሚገባቸው ችግሮች ካሉም ጊዜ ሳንሰጥ ለመፍታት ዝግጁ ነን ብለዋል ፡፡ 

ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው ይህ ብሔራዊ ስታዲም በወንበር ከ62 ሺ  በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም ይኖረዋል ፡፡ 

ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገ ይገኛል ፡፡(የኢፌደሪ ስፖርት ኮሚሽን)

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top